ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በተደረገባቸው ወረዳዎች የስኬታማነት መረጃዎች በሚዲያ ባለሙያዎች በመሰባሰብ ላይ ይገኛል
Back

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ በተደረገባቸው ወረዳዎች የስኬታማነት መረጃዎች በሚዲያ ባለሙያዎች በመሰባሰብ ላይ ይገኛል

ECTA
5 min read

መቱ

ነሃሴ 01/2017 ዓ.ም

የEU-Desira ፕሮጀክት ተግባራዊ በሆነባቸው ወረዳዎች በተጨባጭ በተገኙ ውጤቶችና የፕሮጀክቱን ስኬታማነት በተመለከተ በሚዲያ ባለሙያዎች በኩል መረጃዎች በመሰባሰብ ላይ ይገኛል ።

በህብረት ሀገራቱ የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረግለት ይኽው ፕሮጀክት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል በኢሉአባቦር እና በቡኖ በደሌ ዞኖች በስድስት ወረዳዎች ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በዋናነትም ዘላቂ የቡና ልማት ስራው እና የደን ስነምህዳራዊ ጥበቃው በተቀናጀ የመሬት ማኔጅመንትና የአየር ንብረት አጠባበቅ ስራዎች በአግባቡ መደገፍ ዋነኛው ትኩረቱ መሆኑን ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክ/ዋና ዳይሬክተር እና የልማት ዘርፍ ሀላፊ ጠቁመዋል ።

የመሬት መራቆት እና የጫካ ምንጣሮ የአፈር መሸርሸርን ከማስከተሉም በተጨማሪ የአካባቢያዊ ጥበቃ ስራን እንደሚጎዳ እና ዘላቂነት የሌለው የጫካ ቡና ልማት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል ያሉት ምክ/ዋና ዳይሬክተሩ፤ ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በስፋት የሚገኘው የጫካ ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ በተመዘገበው የያዮ ጥብቅ ደን ውስጥ የሚለማ በመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ ከጫካውም ሆነ ከቡና ልማቱ ማግኘት ያለበትን ጥቅም በአግባቡ ማግኘት እንዲችል ከፍተኛ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ እና በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈቃዱ ደፈረስ በኩላቸው ባለስልጣን መ/ቤቱ በፕሮጀክቱ በኩል

በርካታ ድጋፎች እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው ስለ ፕሮጀክቱ የበለጠ ግንዛቤ ለመፍጠር እና በተጨባጭ ስለተገኙ ስኬታማ ስራዎች ከሚዲያ አካላት ጋር በመሆን መረጃዎችን በማሰባሰብ ለህዝብ እና ባለድርሻ አካላት ተደራሽ የማድረግ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል ።

በተለያየ ሁኔታ የቡናውን ዘርፍ የሚደግፉ በርካታ ፕሮጀክቶች እንዳሉ የገለፁት አቶ ፍቃዱ የEU-Desira ፕሮጀክት ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር በመቀናጀት አነስተኛ ደረጃ አርሶአደሮችን፣ሴቶችን እና ወጣቶችን በመደገፍ ባስገኘው ለውጥ እና ለቡናው ሴክተር ውጤታማነት በአበረከተው አስተዋጽኦ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ስራ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ቡድን በቦታው ተገኝቶ ዘግቧል።

Tags

#ecta#news