የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ2018 የስራ ዘመን ከቡና፣ ሻይና ቅ/ቅመም ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለጸ!!
Back

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ2018 የስራ ዘመን ከቡና፣ ሻይና ቅ/ቅመም ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለጸ!!

Ecta
5 min read

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ2018 የስራ ዘመን ከቡና፣ ሻይና ቅ/ቅመም ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገለጸ!!

በፌዴራሉ፣ በክልሎች እና ባለድርሻ አካላት መካከል የነበረው መቀራረብ እና የጋራ እንቅስቃሴም የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተጠቁሟል!!

ሀምሌ 24/2017

አዳማ

ይህ የተገለጸው በዛሬው እለት የፌዴራሉ፣ የክልል እና የምርምር ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድ ቀርቦ በአዳማ ከተማ ሲገመገም እና ውይይት ሲካሂድበት በዋለበት ወቅት ነው፡፡ 

ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በቦታው ተገኝተው መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት በኢትዮጵያ የቡና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 470ሺህ ቶን ቡና በመላክ ከ2.65 ቢሊየን ዶላር በላይ የተገኘበት አመት መሆኑን ሳበስር ታላቅ ክብር እና ኩራት ይሰማኛል ብለዋል፡፡ ይህ አኩሪ ውጤት የተገኘው ደግሞ መንግስት፣ ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች፣ አ/አደሮች፣ አልሚዎች፣ ላኪዎች፣ አቅራቢዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ እና የተናበበ ጥረት በመሆኑ ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ 

ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉም በተያዘው በጀት አመት ከ600ሺህ ቶን ቡና ለገበያ በማቅረብ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት መታቀዱን እና ለዚህም ቀደም ሲል የነበረው ተቀራርቦ የመስራት እና የጋራ እንቅስቃሴ በበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር በባለስልጣን መ/ቤቱ ምክ/ዋና ዳይሬክተር እና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ቡና ለመላው አለም ለማስተዋወቅ የሚያስችል ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ እና የገበያ መዳረሻዎችንም ቀደም ሲል ከነበሩበት 60 ወደ 84 ከፍ ማድረግ መቻሉን ጠቁመው፤ ቡናችንን በጥራት እና በመጠን ከፍ አድርገን ለአለም ገበያ ማቅረብ ከቻልን ከእቅዳችንም በላይ መሄድ እንደምንችል መገመት ይቻላል ብለዋል፡፡

ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ በባለስልጣን መ/ቤቱ ምክ/ዋና ዳይሬክተር እና የልማት ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት ከሶስት እና አራት አመታት በፊት የተጎነደሉ እና የታደሱ የቡና ዛፎች ምርት መስጠት የሚጀምሩበት ደረጃ ላይ በመድረሳቸው ያቀድነውን እቅድ ለመሳካት ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖራቸው ጠቁመዋል፡፡

አቶ ቦንሳ መርጋ በባለስልጣን መ/ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት በቡና፣ ሻይና ቅ/ቅመም 2017 የነበረው አፈጻጸም ከ2016ቱ ጋር ሲነጻጸር በመጠንም ሆነ በገቢ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት እና ታሪካዊ መሆኑን አስረድተው፤ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ ጭማሪ የታየበት እንደሆነ፣ ጠቁመዋል፡፡ አቶ ቦንሳ በሪፖርታቸው ላይ አያይዘው በግብዓት አቅርቦት፣ በኢንዱስትሪ ግብዓት፣ በቴክኖሎጂ፣ በሎጂስቲክስ፣ እሴት ጭመራ ወዘተ. የተሸለ ምርት እና ገቢ እንዲገኝ ስትራቴጂ ተነድፎ ያንን ለማሳካት ጥረት እየተደረገ እንደሚገን አብራርተዋል፡፡

ሪፖርቱ ከቀረበ በኋላም ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል ።

በመጨረሻም ክቡር ዋና ዳይሬክተር በተለይ ለክልል የስራ ኃላፊዎች ባቀረቡት ጥሪ፤ EUDR/ አውሮፓ ህብረት ያወጣውን ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የሆነ ምርት የመግዛት መመሪያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ፣ በሳይንሳዊ መረጃ ላይ የተመሰረተ፣ በጥራትም ሆነ በመጠን ከፍ ያለ ቡና ወደ ገበያ በማቅረብ በአውሮፓ ማህበረሰብ ተቀባይነታችንን መጨመር እና ያለንን የገበያ ድርሻ የበለጠ ከፍ ማድረግ እንዲቻል የተጠናከረ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያም የበለጠ አጋርነትን ለማጠናከር እና ለተገኙት ውጤቶች ደስታን ለመግለጽ የኬክ መቁረስ ስነስርዓት ተካሂዷል።

መረጃዎቻችንን፦

በፌስቡክ፡- @ethiocta

በቴሌግራም፡- https://t.me/ECTAuthority

በድረገጽ፡- https://www.etiocta.gov.et

ዩቲዩብ፡-  https://www.youtube.com/@ethiopiancoffeeandteaautho1042

ተከታተሉን::  እናመሠግናለን

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#export#accomplishment#eudr#coffee#3billion