የቡና ምርትን ለማሳደግ የተሰጠው ትኩረት የላቀ ውጤት እያመጣ ነው - አቶ አዲሱ አረጋ
Back

የቡና ምርትን ለማሳደግ የተሰጠው ትኩረት የላቀ ውጤት እያመጣ ነው - አቶ አዲሱ አረጋ

ECTA
5 min read

ጳጉሜን 1፣ 2017 የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሰጠው ትኩረት የላቀ ውጤት እያመጣ ነው አሉ።

ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በመገኘት በቀርጫንሼ ግሩፕ የለማውን የቡና ተክል ተመልክተዋል።

ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት ማብራሪያ ለቡና ልማት በመንግስት ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፤ ይህም የቡና ምርትን በማሳደግ ረገው የላቀ ውጤት እያመጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በቀርጫንሼ ግሩፕ የቡና ልማት የውጤቱ ማሳያ መሆኑን አንስተው፤ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘው ይህ የቡና ልማት የጥራትና ምርታማነት ጥሩ ተሞክሮ የታየበት ነው ብለዋል።

ተመሳሳይ ልማት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የቀርጫንሼ ግሩፕ ሥራ አስኬያጅ እስራኤል ደገፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በመንግስት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ለውጤታማነት እንዳበቃቸው እና በጥራትና ምርታማነት ላይ ስኬት መመዝገቡን ተናግረዋል።

በገላና ወረዳ ቡናን ከጥላ ዛፍ ውጭ የማልማት ተግባር ከ750 ሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ መከናወኑንም ጠቁመዋል።

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#coffee#export#development