Source: ቅዳሜ ገበያ
01/08/2025
2
በ2017 ዓ.ም ከጠቅላላው የወጪ ንግድ 8.3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ አፈጻጸሙም በ2016 በጀት ዓመት ከተገኘው 3.71 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ጋር ሲነፃፀር የ4.59 በሊዮን የአሜሪካን ዶላር (123.78%) ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡
ሚኒስቴሩ አክለውም ከ8.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት መንደር ተገንብቶ 5 ጥራት አስጠባቂ ተቋማትን በአንድ ቦታ በመያዝና ተወዳዳሪነታችንን በማሳዳግ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ እና ቀጣናዊ ውህደት እና ዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነት ከማጎለበት አንጻር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊነት ብሔራዊ የትግበራ ኮሚቴ በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በ2018 በጀት ዓመት እነዚህ ስኬቶቻችንን በማላቅ ሌሎች አዳዲስ ድሎችን የምናስመዘግብበት ይሆናል ብለዋል፡፡ በተለይ በኢ-ንግድ ተቋማዊ መዋቅርን የተደራጀ ሲሆን ሲሆን ለዘመናዊ ግብይት መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ስራ እንደሚከናወን አስገንዝበዋል፡፡