ኢትዮጵያና ብራዚል የንግድ ትብብራቸውን የሚያጠናክሩበት ፎረም በመስከረም ወር ይካሄዳል ተባለ
Back

ኢትዮጵያና ብራዚል የንግድ ትብብራቸውን የሚያጠናክሩበት ፎረም በመስከረም ወር ይካሄዳል ተባለ

ABN
5 min read

በሚቀጥለው ዓመት መስከረም 16-18 ቀን 2018 ዓ.ም በሳኦ ፓውሎ የኢትዮጵያ እና ብራዚል የንግድና ቱሪዝም ፎረም እንደሚካሄድና በፎረሙ ከሁለቱም ሀገራት ብዙ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ልዑልሰገድ ታደሰ ገለጹ፡፡  አምባሳደሩ አክለውም ፎረሙ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝም እና በቴክኖሎጂ ልውውጥ ዘርፎች በኢትዮጵያና በብራዚል መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ይረዳል፡፡ ኢትዮጵያ የብሪክስን አባልነት ተጠቅማ ከብራዚል ጋር ያላትን የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር ለማጠናከር እየሰራች መሆኑንና ከደቡብ-ደቡብ ትብብር ጋር በተያያዘም የበኩሏን እየተወጣች መሆኑን አስረድተዋል፡፡ 

Image

ፎረሙ ላይ በኢትዮጵያ መንግስት ቅድሚያ በተሰጣቸው የግብርና፣ የማዕድን፣ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝም እና የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የብራዚል ባለሃብቶችና ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል፡፡ አምባሳደሩ፣ ከዚህ በፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካሄዱ የንግድና የኢንቨስትመንት ፎረሞች የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር ጥሩ አጋጣሚዎች መፍጠራቸውን አስታውሰዋል፡፡ የብራዚል ባለሃብቶችም ቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናቶችን ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ መሆኑንም አክለዋል፡፡ በብራዚል ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ መሰረት፣ የኢትዮጵያና የብራዚል የዲፕሎማቲክ ግንኙነት በ2026 የ75ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ያከብራል። ሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን በ1951 ዓ.ም መስርተዋል

Tags

#news#brazil#ecta#ethiopia