ቻይና 183 አዳዲስ የብራዚል ቡና ኩባንያዎች ወደ ገበያዋ እንዲገቡ መፍቀዷን አስታወቀች።
Back

ቻይና 183 አዳዲስ የብራዚል ቡና ኩባንያዎች ወደ ገበያዋ እንዲገቡ መፍቀዷን አስታወቀች።

ECTA
5 min read

China welcomes 183 Brazil coffee sellers in wake of US tariffs

By Ana Mano

August 3, 20255:44 PM GMT

የአሜሪካ መንግስት በብራዚል ቡና ላይ 50% የሚደርስ ከፍተኛ የቀረጥ ጭማሪ ማድረጉን ካስታወቀ ከቀናት በኋላ ነው በቻይና መንግስት በኩል ይህ ፈቃድ የተሰጠው፡፡ እርምጃው በሁለቱ የዓለም ግዙፍ ኢኮኖሚዎች መካከል ያለውን የንግድ ፉክክር በድጋሚ አሳይቷል፡፡ ነገሩ ለብራዚል ቡና ላኪዎች ትልቅ እፎይታን እንደሚሰጥ ይገመታል።

ብራዚል በየዓመቱ 8 ሚሊዮን ከረጢት (bags) የሚጠጋ ቡና ለአሜሪካ ገበያ የምታቀርብ ሲሆን፣ ይህም ባለፉት 12 ወራት ብቻ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ነበረው።  የአሜሪካ መንግስት የጣለው 50% ቀረጥ፣ ከኦገስት 6 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን፣ ለብራዚል ቡና ላኪዎች ትልቅ ፈተናን ይዞ በመምጣቱና የአገሪቱን ግዙፍ ገበያ በእጅጉ ስለሚጎዳው፣ የብራዚል ላኪዎች በአስቸኳይ አማራጭ ገበያዎችን መፈለግ አስገድዷቸዋል።

ቻይና፣ ብራዚል በገባችበት ችግር ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ገበያዋን በፍጥነት ክፍት አድርጋለች።

አዲሱ የኤክስፖርት ፈቃድ ለአምስት ዓመታት ጸንቶ እንደሚቆይ የተገለጸ ሲሆን የቻይና ውሳኔ ይፋ የሆነው በብራዚል የቻይና ኤምባሲ ማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ ነው፡፡ 

አጋጣሚው ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖራትን የቡና ገበያ አማራጭ አያሰፋውም ትላላችሁ? በቻይና በስፋት እየሄድንበት ያለው የገበያ ሁኔታ ደግሞ የበለጠ እንድንገፋበት እና ፉክክሩም የላቀ ሊሆን እንደሚችል ያሳያል ብለን እንገምታለን፡፡

SAO PAULO, Aug 3 (Reuters) - China has approved 183 new Brazilian coffee companies to export products to the Chinese market, according to a social media post of the Chinese embassy in Brazil on Saturday.

The measure, a boon to local exporters after the United States government's announcement of steep tariffs on Brazilian coffee and other products, took effect on July 30.

The new Chinese export permits are valid for five years, according to the post. The U.S.'s 50% tariff on some Brazilian products will begin on August 6.

The levy represents a challenge for commodities traders and Brazilian coffee exporters, who need to find alternatives for the roughly 8 million bags sold to U.S. coffee processors every year.

China is Brazil's top trade partner overall while the U.S. is a big buyer of Brazilian beef and orange juice, among other products.

In June, Brazilian coffee exports into the U.S. totaled 440,034 60-kilo bags, 7,87 times more than Brazil's sales into China of nearly 56,000 bags that month, according to trade data compiled by industry lobby Cecafe.

Tags

#china#brazil#coffee#tariff