"በተሳለጠ ንግድ ወደ ሚጨበጥ ሀገራዊ ተስፋ"
በሚል መሪቃል ሀገራዊ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሴክተር ጉባዔ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩተረ ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በመካኼድ ላይ ይገኛል።
ጉባዔውን የከፈቱት ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ የንግደና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስትር ጉባዔተኞችን እንኳን ደኅና መጣችኹ መልዕክት አስተላልፈው።
በ2017 በጀት ዓመት በንግዱ ዘርፍ ስኬታማ ሥራዎች መከናወናቸውንና እነዚህን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ በወጪ ንገድ 8.3 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱንና ይኽም ታሪካዊና የሀገራችንን ማንሰራራት የሚያበስር አፈጻጸም ነው ብለዋል።
ሚኒስትር መ/ቤቱ የሚከታተላቸው የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ንግድና የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ሰኬታማ አፈጻጸም መመዝገቡን ገልጸዋል። በጥራጥሬና ቅባት እህሎች ከዕቅዱ 90 በመቶ እንዲሁም የቁም እንስሳት የወጪ ንገድ ከ200 በመቶ በላይ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
በቀጣናዊ ትስስር ላይ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመኾን እየተደረጉ ያሉ እልህ አስጨራሽ የድርድር መርሃ ግብሮች ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየደረሰ መኾኑንና የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣናም ሀገራችን በቀጣይ ወራት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ሚኒስትሩ አስታውቃዋል።
በቀጣይ 2018 በጀት ዓመት በላቀ የትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር በመተግበር ስኬታም አፈጻጸም ለማስመዝገብ መስራት እንደሚገባ አሳሰረበዋል
በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮን ጨምሮ የክልል ንግድ ቢሮ ሐላፊዎች ዓመታዊ አፈጻጸምና የቀጣይ አቅጣጫዎችን እያቀረቡ ነው።