***ነሀሴ 12/2017 ዓ.ም.****
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በቅጥር ጊቢው የለሙ የተለያየ ዝርያ ያላቸውን የቡና ችግኞች በማፍላት የዘንድሮውን አረንጓዴ አሻራ እያሳካ መሆኑ ይታወቃል።
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮም የሀገር- ዓቀፉን አረንጓዴ አሻራ መርሀ -ግብር የበለጠ ለማሳካት ከ4000 በላይ የቡና ችግኞችን ተረክቧል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቡና በክልሉ እየለማ ሲሆን ይህንኑ ተግባር ማስፋት አላማው ያደረገ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተሻሻሉ የቡና ዝርያ ችግኞችን ተረክቧል።
ምንጫችን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ነው!!