አዳማ
ሐምሌ 09/2017ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከኦሮሚያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በክልሉ ከሚገኙ የቡና ባለሙያዎች እና ላኪዎች ጋር በቡና ጥራት ዙሪያ ውይይት አድርጓል ።
በመድረኩ የተከበሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ ብሔራዊ ክልል ፕሬዝዳንት እና የተከበሩ አቶ አዲሱ አረጋ የገጠር ልማት ክላስተር ዋና ዳይሬክተር በክብር እንግድነት ተገኝተዋል ።
የተከበሩ ዶክተር አዱኛ ደበላ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የበጀት ዓመቱን የቡና ስራ አፈፃፀም እና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገባቸውን ጉዳዮች ገለፃ አድርገዋል ።ዶክተር አዱኛ አክለውም በበጀት ዓመቱ የተገኘው የቡና ኤክስፖርት ሪከርድ ሊሰበር የቻለው በክልሉ ያሉ የመንግስት እና የግል ተቋማት በቅንጅትና በቁርጠኝነት መስራት በመቻላቸው ነው ካሉ በኋላ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በቀጣይም የተከበሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ አቶ አዲሱ አረጋ እና ዶ/ር አዱኛ ደበላ በጋራ ከመድረኩ ለተነሱ በርካታ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ምላሽ እና ማጠቃለያ ከሰጡ በኋላ ሁነቱ የተጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና የኮ/ን ቡድን በቦታው ተገኝቶ ዘግቦታል።
ተከታተሉን:: እናመሠግናለን