በኡዩዲአር  የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::
Back

በኡዩዲአር የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::

Ethiopian Coffee And Tea Authority
5 min read

ስልጠናው   በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንና  በአውሮፓ ህብረት  የፋይናንስ ድጋፍ  እንደሚካሄድ ታውቋል፡ በስልጠናው ላይ  ከተለያዩ የቡና አብቃይ ክልሎች እና ዞኖች ከዘጠና በላይ  ሰልጣኞች እየተከታተሉት ይገኛሉ፡፡

በአውሮፓ ህብረት የደን ምንጣሮ ህግና ደንብ ዙሪያ በመረጃ  አሰባሰብና በዳታ ቤዝ ማኔጅመንት ለስድስት ቀናት  እየተሰጠ ያለው  የአሰልጣኞች ስልጠና  ዛሬ  ለሶስተኛ ቀን  ቀጥሎ ውሏል ፡ ፡በትናንትናው እለት  በቲዎሪና  በመስክ የተግባር ትምህርት    ሲከታተሉ የዋሉትን ስልጠና  ሰልጣኞቹ  ዛሬ በቡድን በመሆን  በውይይትና  እርስበርስ በመማማር   ስልጠናውን አጠናክረውታል፡፡ የነገውና የቀጣይ ቀናት ስልጠና  በጂፒኤስ  ዳታ  አሰባበሰብ  አጠቃቀምና  በኤስ ደብሊዩ ሞባይል አፕሊኬሽን  እና  በጂኦስፓሻል  መረጃ አሰባሰብ   ላይ  እንደሚሰጥ ታውቋል ፡፡

የኢትዮጵያ ቡናና  ሻይ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና  ኮሙዩኒኬሽን  የስራ ክፍል  እንደዘገበው

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#ethiopian coffee and tea authority#ecta#coffee#eudr