13/12/2017ዣ/ም
ዜና ኢቡሻ
ጂማ
ስልጠናውን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ፡፡ ስልጠናው ነሃሴ 12/2017 ዓም የተጀመረ ሲሆን እስከ ነሃሴ 16/2017 ዓ/ም ለተከታይ ቀናት ይሰጣል ፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው በጂኦ ሎኬሽን ፤ በጂኦስፓሻል ዳታ አሰባሰብ ፤በዳታ ቤዝ ማኔጅመንት እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፤ የአውሮፓ ህብረት ሃገራት ባወጡት በጸረ ደን ምንጣሮ ህግና መመሪያ፤ ከደን ምንጣሮ ነጻ የሆነ የቡና ምርት፤ የደን ጭፍጨፋ እና በአየር ንብረት ለውጥ፤ በደን ምንጣሮና አካባቢያዊ ብዘሃ ህይወት ደህንነት እና የአውሮፓ ህብረት ሃገራት ባወጡት የጸረ ደን ምንጣሮ አስገዳጅ የህግ ማእቀፍ በሚሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ያተኮረ ነው ፡፡
በዚህ ለአንድ ሳምንት ለተከታይ ቀናት በሚሰጠው ስልጠና ከተለያዩ ክልሎችና ዞኖች የመጡ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ የቡና አምራቾች የቡና አልሚዎች የቡና አቅራቢዎች እና የቡና ላኪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ስልጠናው በትናንትናው እለት በወይዘሮ ሃዊ አቶምሳ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ በእንኳን ደህና መጣችሁ የመክፈቻ ንግግር ተጀምራል ፡፡
በደን ምንነትና ከቡና ተክል ጋር ያለው ተዛምዶ ፤ የአውሮፓ ህብረት ሃገራት ከደን ምንጣሮ ነጻ ምርት አስገዳጅ ህጎች እና መመሪያዎች ፤ህጉና መመሪያው በስራ ላይ የሚጀመርበት ጊዜና አፈጻጸም በዶክተር ዘሪሁን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ National Coffee Plat form አማካሪ እና አስተባባሪ የአውሮፓ ህብረት ሃገራት የጸረደን ምንጣሮ ህግና መመሪያ በሰፊው ተብራርቷል ፡፡ ወደ አውሮፓ ህብረት ሃገራት የቡና ገበያ ግንኙነት ያላችሁና ቡናችሁን ወደነዚህ ሃገራት ለመላክ የምትፈልጉ እና ደንበኝነታችሁን በዘላቂነት ማስቀጠል ፍላጎት ያላችሁ ቡና ላኪዎች የቡና አምራቾችና ቡና አልሚዎች የህብረቱን ሃገራት የህግ ማእቀፍ ተግባራዊ አድርጋችሁ እንድትንቀሳቀሱ ከወዲሁ መዘጋጀት ይገባችኋል በማለት ዶክተር ዘሪሁን ለሰልጣኞቹ ነግረዋቸዋል ፡፡
በጂኦስፓሻል ዳታ አሰባሰብና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፤በዳታ ማኔጅመንት፤ በቡና ዱካ መነሻና መዳረሻ ዙሪያ ዳታ እንዴት እንደሚሰበሰብ እና የዳታ መረጃ ጠቀሜታ በሚሉ ሁነኛ ሃሳቦች ዙሪያ ስልጠናውን የሰጡት ደግሞ ወይዘሮ ሃዊ አቶምሳ ናቸው ፡፡
ከኢትዮጵያ የህዋ ሳይንስ ምርምር ተቋም የመጡት ዶክተር ብርሃን በበኩላቸው በጂኦ ሎኬሽን ዳታ አስፈላጊነት ፤ የአውሮፓ ህብረት ሃገራት የጸረ ደን ምንጣሮ ህግና መመሪያ ለምን ? ፤ አባል ሃገራቱ ባስቀመጡት ቡና አምራች ሃገራት ሪስክ አሰስመንት እና በግሎባል እና በሎካል ጂኦግራፊ ሰርቬይ አሰባሰብ ጠቀሜታ ልዩነትና አንድነት “ በሰፊው ለሰልጣኖቹ አብራርተው፡ በስፓሻል በአትሪቢውትና በሜታ ዳታ አሰባሰብ ቴክኒክ እንዲሁም አንድነትና ልዩነታቸው ፤ በጂፒኤስ እና በጂአይ ኤስ ዳታ የመሰብሰቢያ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያም ጭምር ዶክተር ብርሃን በሰፊው ነግረዋቸዋል ፡፡
በእለቱ ከሰልጣኞቹ በተነሱ አስተያየቶችና ስልጠናዎች ዙሪያ አሰልጣኞቹ ማብረራሪያና መልስ ሰጥውበታል፡፡
የኢቡሻ ባለስልጣን የህ /ግ/እና ኮሙዩኒኬሽን እንደዘገበው