በቡናው ዘርፍ ለተሰማሩ አካል ጉዳተኞች ትኩረት መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ስልጠና ተካሄደ
Back

በቡናው ዘርፍ ለተሰማሩ አካል ጉዳተኞች ትኩረት መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ስልጠና ተካሄደ

ECTA
5 min read

ነሀሴ 20/2017 

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በGIZ ከሚደገፈው እና Light for the world ከተሰኘ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በቡናው ዘርፍ ለተሰማሩ አካል ጉዳተኞች ትኩረት መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በአዳማ ከተማ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡ ስልጠናውን በመስጠት ላይ የሚገኙት ደግሞ Light for the world ፕሮጀክት በተለያየ የሀላፊነት ደረጃ ላይ በሚገኙ እና የካበተ ልምድ ባላቸው አካል ጉዳተኛ ባለሙያዎች አማካኝነት ነው፡፡ 

በስልጠናው መክፈቻ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክ/ዋና ዳ/ር እንዳሉት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለ ኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ምጣኔ የተጠኑ ጥናቶች ግን 17.6 በመቶ ሕዝቧ ከአካል ጉዳት ጋር እንደሚኖሩ ያሳያል ብለዋል።

ከአካል ጉዳት ጋር ለሚኖሩ ሰዎች መሠረታዊው ፈተና አካል ጉዳተኛ መኾናቸው ሳይኾን፣ ኅብረተሰቡ ስለ አካል ጉዳተኝነት ያለው ግንዛቤ መኾኑን በአጽንኦት የገለጹት አቶ ታጋይ፣ በዚህም የተነሣ አብዛኞቹ አካል ጉዳተኞች ፍጹም ድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ አመልክተዋል።

ስለኾነም ኅብረተሰቡ አካል ጉዳተኝነትን የተለየ አድርጎ ማሰብ እንደሌለበት፣ የአካል ጉዳተኛ መብቶችን ማክበር እና የሚገባቸውን ድርሻ ማካፈል ከሁላችንም የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ከአካል ጉዳተኝነት ጋር በተያያዘ ያሉ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ ብሎም ሀገራዊ የሕግ ማእቀፎችን ዘርዝረው አስረድተዋል። በየመሥሪያ ቤቶች እና ተቋማት አካል ጉዳተኞችን ማካተት የግድ እንደኾነ እና ማግለልን መዋጋት የኹሉም ዜጋ ግዴታ መኾኑንም ጠቁመዋል።

አቶ መላኩ ተክሌ የፕሮጀክቱ ሀላፊ በበኩላቸው እንዳሉት በአገራችን 17.6 በመቶ የሚገመቱ አካል ጉዳተኞች መኖራቸውን እና ከነዚህ ውስጥ ደግሞ 90 በመቶ የሚሆኑት ኑሯቸው በገጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከተፈጥሮ በተጨማሪ ማንኛውም ሰው በማንኛውም ሰአት ሊያጋጥመው በሚችለው ጉዳት ሊከሰት የሚችል መሆኑን የጠቆሙት አቶ መላኩ፣ በግብርናው ዘርፍም ሆነ ሌላ በማናቸውም ዘርፍ የሚሰራ አካል ሙሉ ለሙሉ የሚመለከተው መሆኑን አስረድተዋል፡፡  አካል ጉዳተኞች በየትኛውም ዘርፍ ተሰማርተው መስራት የሚችሉ በመሆናቸውም በአካል ጉዳተኛ ጉዳተኝነት ዙሪያ በማህበረሰቡ ዘንድ ያለ ግንዛቤ በማሳደግ በሚዘጋጁ ማናቸውም ፕሮግራሞች እና እቅዶች ውስጥ ማካተት ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመምከርም ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የዋና ዳ/ር ጽ/ቤት ኃላፊ በንግግራቸው እንዳነሱት ከእስከዛሬው ለየት ባለ መልኩ በአካል ጉዳተኝነት ዙሪያ ለመነጋገርና በሚዘጋጁ እቅዶች እንዴት ማካተት ይቻላል በሚለው ጉዳይ ለመምከር መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ አካል ጉዳተኛ በተመለከተ በአለማቀፍ ሰብአዊ መብቶች ላይ በግልጽ የተመላከተ እና ሊከበር የሚገባው መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ አብዛኛው ማህበረሰብ ዘንድ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በጉዳዩ ላይ የግንዛቤ ችግሮች መኖራቸውን እና አሁንም ድረስ ሙሉ በሙሉ ተቀርፏል ለማለት እንደማይቻል አስረድተዋል፡፡ በግብርናው ዘርፍ በተለይ በቡና ዙሪያ የተሰማሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በመኖራቸው ያሉባቸውን ችግሮች ቀርቦ ለመረዳት እና ለወደፊት ችግሮቻቸው የሚቀረፉበትን ሁኔታ ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር ለመፍታት የመድረኩ ወሳኝነት ጠቁመዋል፡፡

በሁለት ቀናቱ ስልጠና ላይ በርካታ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን ከጅማ አጋሮ የመጡ አርሶ አደር ከአካል ጉዳተኝነት ጋር በተያያዘ የሚገጥሙ ችግሮችን በተመለከተ ሰፋ ያለ ልምዳቸውን አካፍለዋል።

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#coffee