በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል ተግባር የተሰማሩ 138 ተጠሪጣሪዎች ባንክ ሒሳብ ታገደ
Back

በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል ተግባር የተሰማሩ 138 ተጠሪጣሪዎች ባንክ ሒሳብ ታገደ

አዲስ ስታንዳርድ
5 min read

Source: 

09/08/2025

"ሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓትን ወደ ጎን በመተው በሕገ ወጥ እና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች" የባንክ ሒሳብ መታገዱን የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ገለፀ፡፡ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት በሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓት በኩል እንዲከናወን በግልጽ የተቀመጠ መሆኑ በህገ ወጥ መጠቀም የንብረት መወረስን ጨምሮ በከፍተኛ ጽኑ እስራት እንደሚያሰቀጣ አሳስቧል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀልን እንደ መደበኛ የንግድ ስራ በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በመሆናቸው ክትትል ሲደረግባቸው መቆየቱን አገልግሎቱ ለኢዜአ ገልጿል፡፡

በዚህ መሠረትም ክትትል ተደርጎ የተደረሰባቸው እና በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ላይ የተሰማሩ 138 ዋነኛ ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ ተደርጓል ነው ያለው፡፡ ይህ የተገለፀው የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ኢመደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን የሚጠቀሙ የንግዱ ማህበረሰብ ገንዘባቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ መግለፃቸውን ተከትሎ ነው። አቶ ማሞ ብሔራዊ ባንክ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸው “የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ተማኝነትን ሆነ ብሎ ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋን ለማዛባት በማለም መቀመጫቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ህገ ወጥ የገንዝብ ዝውውር አስተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚቀጥል” ገልጸዋል

Tags

#blackmarket#nationalbank