ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ እና የባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂደ
Back

ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ እና የባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂደ

Ethiopian coffee and tea authority
5 min read

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

ኢቡሻባ፤

የኢትዮጵያ ቡና ሻይ ባለስልጣን የስራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ እና የባለስልጣኑ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ሰነዱን ያቀረቡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ ዶ/ር አዱኛ ደበላ እንደመንደርደሪያ በባለፈው በጀት ዓመት የተመዘገበው የ2.6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አፈጻጸም ከምንግዜውም በላይ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ጀምሮ እጅግ አድናቆት እንደተቸረው በመግለጽ ጀምረዋል፡፡ ይህም ውጤት የጋራ ጥረት ውጤት እንደሆነና ለዚህም የባለስልጣኑንና እስከ ክልል መዋቅር ያሉት አመራርና ሠራተኛውን ጨምሮ መላ የቡና ተዋናዩን በማመስገን አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

በማስከተል የ2017 በጀት አመት የማክሮ ኢኖሚና የባለስልጣኑን ዕቅድ አፈጻጸምን ወደ ማቅረብ በማምራት አጠቃላይ ዓለማቀፍ የምርትና ገበያ ሁኔታ በማስቀደም ጀምረዋል፡፡ ሲያቀርቡም የግብይት ሁኔታ በአሜሪካ እየቀነሰ  እንደመጣና በአንጻሩ ደግሞ በመካከለኛ ምስራቅና በቻይና ዕድገት እያሳየ እንደመጣ አውስተዋል፡፡ ከ2019 እስከ 2022 ድረስ ዓለማቀፍ የንግድ አዝማሚያ ጭማሪ እያሳየ እንደመጣና ከዚያ በኋላ እስከ 2024 ድረስ ጭማሪ ሳያሳይ ወጥ እድገት እንደተስተዋለ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ምክንያት ሆነው እሚጠቀሱት የነዳጅ ዋጋ መቀነስና የማዳበሪያ ዋጋ መጨመር እንዲሁም የገንዘብ የመግዛት አቅም መውረድ እንደሆነ አክለው ገልጸዋል፡፡ ዓለማቀፍ የቡና ዋጋን አስመልክቶም ሲያቀርቡ ለአንድ ቶን በአማካይ 7 ዶላር ሆኖ እንደቆየና 2025 ላይ 8 ዶላር በአማካይ እንደደረሰ፤ በ2026 ግን ሊቀንስ ይችላ ተብሎ እንደሚታሰብ ተናግረዋል፡፡ በአሜሪካን የግብር መጫን ምክንያት የኤክስፖር እድገት እንደቀነሰ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ በአውሮፓም መቀነስ ሲስተዋል በኤዢያ ግን ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል፡፡ 

አንደሀገር ያለውን ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ በጀት አመት ዕቅድም ሲያቀርቡ ወደ 9.4 ቢሊዮን ዶላር ከሸቀጦች የውጭ ንግድ የሀገሪቱን ገቢ ለማሳደግ እንደታቀደና ከዚህ ውስጥ 3 ቢሊዮን ዶላር ከቡና ለማስገኘት እንደታቀደ አሳውቀዋል፡፡ ይህ ምን ያህል የቡናው ዘርፍ ወሳኝ እንደሆነና ከወርቅ ሚና ጋር በመፎካከር ለሀገሪቱ ወሳኝ እንደሆነ መገንዘብ እንደሚገባና ለስኬቱም ምን፦ ያህል ኃላፊነት እንደተጣለብን መገንዘብ ይቻላ ብለዋል፡፡ አጠቃላይ ከግብርና 4 ቢሊዮን ዶላር አንደተገኘና በያዝነው በጀት አመት ወደ 4.7 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ እንደታቀደ ገልጸዋል፡፡ 

እንደባለስልጣኑ ያለውን አፈጻጸምና ዕቅድ ሲያቀርቡም በቡናው ረገድ  4600 በላይ ቡና ተልኮ 2.6 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱ ከዚህ ቀደምም ሲወሳ እንደመጣ አስታውሰው የሚታረስ መሬት ከ32 ሚሊዮን ሄክታር ወደ 33 ሚሊዮን ሄክታር ለማሳደግ እንደታቀደ ገልጸው በያዝነው በጀት አመት 600 ሺ ቶን ቡና በመላክ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማስገኘት ታቅዷል ብለዋል። እንደቡናው ሁሉ የሻይና ቅመማቅመም አፈጻጸምንና ዕቅድን አቅርበዋል።

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#ecta#2018#export