የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ በኦንላይን ሆነ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚሰጠውን የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባ እና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎት ከታህሳስ 06/2018 ጀምሮ ኦንላይን ማድረጉን የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብዱልሀኪም ሙሉ አስታወቁ።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለንግዱ ማኅበረሰብ የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በማዘመን ረገድ ሌላ ወሳኝ እርምጃ መውሰዱን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው በዚህም የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎት ከዚህ በፊት በማኑዋል ሲሰጥ ከነበረበት ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ሥርዓት መሸጋገሩን ገልጸዋል።
ይህንን አሰራር በማዘመን የተደረገው ማሻሻያ ላኪዎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ከሰው ንክኪ ነጻ በሆነ መልኩ ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲያገኙ የሚያስችል በመሆኑ የአገልግሎቱን ተደራሽነት ከፍ ያደርገዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ፣ የተገልጋዮችን ጊዜና ወጪ ቆጣቢ እንዲሆኑ እያደረገ ሲሆን ንግድ ተደራሽ፣ ዘመናዊና ፍትሐዊ እንዲሆን የአሰራር ማሻሻያዎች በስፋት እየተደረጉ ነው።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከታህሳስ 06/2018 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገውን የውል ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ መገልገያ በየነ መረብ(export.etrade.gov.et) አጠቃቀም በተመለከተ በዛሬው እለት ለላኪዎች ስልጠና ሰቷል፡፡




