የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የወጪ ንግድ አፈጻጸምና ቀጣይ የክንውን አቅጣጫ ላይ ከላኪዎች ገንቢ ውይይት አድርገዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በበጀት አመቱ ባለፋት ሰባት ወራት ከወጪ ንግድ 5.91 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል።
አፈጻጸሙ የዕቅዱ 117 በመቶ ክንውን መሆኑንም ገልጸዋል። ይህ ግኝት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 65 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
በበጀት ዓመቱ ለማሳካት ከታቀደው 9.4 ቢሊየን ዶላር አልቆ ለመፈጸም ለመፈጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በቀሪ ወራት ከፍተኛ ርብርብ እንደሚደረግም ክቡር ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
በሚኒስተር መስሪያቤትችን የወጪ ንግድን ለማሳለጥ ከተገበርናቸው የአሰራር ማሻሻያዎች የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና የመላኪያ ፈቃድ አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ሥርዓት ማሸጋገሩ ላኪዎች የትም ሆነው ስራቸውን እንዲያቀላጥፋ በማስቻሉ በተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ላኪዎች አረጋግጠዋል።
በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ሊወሰዱ የሚገቡ እርምጃዎችን በተመለከተ የሃገራችንን ጥቅም ማዕከል ያደረጉ የትኩረት አቅጣጫዎችን ተቀምጠዋል።
በዚህም መሰረት ላኪዎች ምርትን መከዘን አቁመው በወቅቱ ወደ ገበያ በማውጣት በአለም አቀፍ ገበያ የሚገባንን ሃገራዊ ፋይዳ እንዲያስጠብቁ ክቡር ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የምርት ጥራትን ለማሳደና የገበያ መሰረት ልማት ስብራቶችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ርብርብ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለዚህም በመላው ሃገሪቱ በመገንባት ላይ የሚገኙ አስር የሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ማዕከላት ተጠቃሽ መሆናቸውን ክቡር ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።







