የውጭ ንግድ ገቢ ሪፖርት
Back

የውጭ ንግድ ገቢ ሪፖርት

Motri
5 min read

በስምንት ወራት ውስጥ ከ6.7 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ንግድ ገቢ ተገኘ።

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 5.83 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ፣ 6.76 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት መቻሉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት፤ የዘንድሮው አፈጻጸም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ2.4 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ50 በመቶ ብልጫ አለው።

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ከፍተኛ አፈጻጸም የታየባቸው ዘርፎች ማዕድን (149.44%)፣ ኤሌክትሪክና ሌሎች (112.35%)፣ ግብርና (90.53%) እና ማኑፋክቸሪንግ (87.68%) ናቸው። ሚኒስቴሩ በቀጥታ ከሚከታተላቸው የወጪ ንግድ ምርቶችም 606.8 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ፣ 527.9 ሚሊዮን ዶላር ወይም የዕቅዱን 87 በመቶ ማሳካት ተችሏል።

የዚህ ስኬት ዋና ምንጮች፦

* በሀገሪቱ የተወሰደው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምርትና ምርታማነትን ማሳደጉ፣

* የገበያ መዳረሻዎችን የማስፋት ሥራ መሠራቱ፣

* በሕገ-ወጥ የምርት ክምችት ላይ የተደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን መጠን መጨመሩ፣

* የማነጻጸሪያ ዋጋ ተመን በዓለም አቀፍ የገበያ ዋጋ ልዋዋጭነት መሠረት በየወቅቱ ክለሳ የምደረግ እንደሆነ ክቡር ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

#Ethiopia_Motri

Gallery

Gallery image 1

Tags

#Motri#coffee