የውጭ ምንዛሪ ምንጭ እየሆነ የመጣው የሮዝመሪ ምርት በየም ዞን ፎፋ ወረዳ፦
ጥቅምት፣23/2018ዓ.ም
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን ፎፋ ወረዳ ለኢኮኖሚ ብልፅግና ጉዞ ስኬትና የላቄ ፋየዳ ያለው ለውጭ ምንዛሪ ምንጭ እየሆነ የመጣው የሮዝመሪ ምርት ማሳ በከፊል።
ከዚህ ቀደም በሀገር ቤት ለስጋ መጥበሻና ለተለያዩ የምግብ ማጣፈጫነት ብቻ እያገለገለ ያለው ሮዝመሪ፤ በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃም ተፈላጊነቱ እያደገ መጥቷል።
ሮዝመሪ አማራጭ የገቢ ምንጭ ከመሆኑ ባለፈ በተጎዳና በአሲዳማነት በተጠቃ መሬት ላይ በመልማት የመሬቱን ጤንነት የመመለስ አቅም ያለው መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።
ግብርና ካሉት 6ቱ የግብርና ሴክተር ምሶሶዎች ከሆነው የውጭ ምርትንን ማምረትና የውጭ ምርት በሀገር ውስጥ መተካት ሲሆን የሮዝመሪን ምርት ፋይዳው የላቀ ነው።
