የስትራቴጂ ሰነድ ርክክብ ተካሄደ
መጋቢት 04/2018
ኢቡሻባ
በጂ አይ ዜድ ፈንድ አድራጊትና በኬር ኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለፍጻሜ የበቃውን የሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ሰነድ 500 ኮፒ ሁለቱ አካላት በጋራ በመሆን ለኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስጣን አስረክበዋል፡፡
በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ ዶ/ር አዱኛ ደበላ እንዳሉት ከአውሮፓ ኅብረት ደንብ ጋር በተያያዘ ብዙ ጉዳዮችን የተከናወኑ እንደሆነ ገልጸው ከሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ጋር በተያያዘ የተኬደው ርቀት ውሱን ሆኖ የቆየ ቢሆንም ከዚህ ስትራቴጂ ሰነድ ጋር በተያያዘ በተደረገው ጥረት ግን ብዙ ስራዎች እንደተከናወኑና ይህ ወሳኝ ሰነድም ግንዛቤን ከማስጨበጥ ባሻገር ብዝበዛውን ለመከላከል በሚደረግ ጥረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም በስራው የተሳተፉትን ጂ አይ ዜድን፣ ኬር ኢትዮጵያን፣ የተቋሙ ስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞችን አመስግነዋል፤ በቀጣይም ይህን ሰነድ ለተፈጻሚነቱ የሚመለከተው አካል መረባረብ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
ከዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት፣ ከዓለማቀፍ የስራ ድርጅት እና ኢፌዴሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከአውሮፓው ደንብ ጋር ተያይዞ ከዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ሕጎች አንጻር ስለ ሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ለቡናው ሴክተር አልሚዎች፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች እና ላኪዎች በአዲስ አበባ፣ ሐዋሳ እና ጅማ ስለጠናዎችን አንደሰጠ ይታወሳል፡፡


