የሸማች መብት ጥበቃ ማህበራትን በማጠናከር የሸማቹን መብትና ጥቅም ማስከበር ይገባል።
=================
አዲስ አበባ ታህሳስ 8/2018 ዓ/ም በክልሎችና ከተማ አስተዳደር የተቋቋሙ የሸማች መብት ጥበቃ ማህበራትን በማጠናከር የሸማቹን መብትና ጥቅም ማስከበር እንደሚገባ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በክልልና ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ በሸማቾች ጥበቃ ላይ ለሚሰሩ የስራ ሂደት እና ለሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበራት አመራሮች እየሰጠ ባለው ስልጠና ላይ ገልጿል።
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሸማቾች መብት ጥበቃና ግንዛቤ ዴስክ በስልጠናው ሁለተኛ ቀን ውሎ በሸማች መብት ጥበቃ ሲቪክ ማህበራት አሰራር ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጠ ሲሆን የተለያዩ ሀገራት የሸማች መብት ጥበቃ ማህበራት ልምድ ተሞክሮ ቀርቧል።
ሲቪክ ማህበራቱ ጉዳዪ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተደጀና በተቀናጀ አግባብ በመስራት ለሸማቹ ህብረተሰብ ግንዛቤ በመፍጠርና በሸማቹ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በመቀነስ ሸማቹን በመወከል ለመብቱና ጥቅም መከበር መሞገት እንደለበት በመድረኩ ተገልጿል።
በመጨረሻም የስልጠና ተሳታፊዎችም በጥራት መንደር ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሚገኙ የገቢና ወጪ ምርቶች ጥራትን የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የፍተሻ ላቦራቶሪዎችን የጎበኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ስለሚሰጣቸው የፍተሻ፣ የኢንስፔክሽንና ሴርተፊኬሽን አገልግሎት ዙሪያ በድርጅቱ የማርኬቲንግና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ተኪኤ ብርሃነ ገለጻ ተደርጓላቸዋል።






