በሀገራችን ለ50ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን የሴቶች ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በዛሬው እለት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት እና የወጪ ንግድ ኮንትራት አስተዳደር አገልግሎትን በሴት ባለሙያዎች ብቻ እየሰጠ ይገኛል፡፡
የሴቶች ቀን የሴቶች ድምጽ የሚሰማበት፣ ጥንካሬያቸው የሚወደስበት እና ለተሻለ እኩልነት ቃል የሚገባበት ነው፡፡ ይህንን ምክንያት በማድረግ በሴት ባለሙያዎች ብቻ እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና ሚኒስትር ዴኤታዎች ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ውሀብረቢ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በንግዱ ዘርፍ ተሰማርተው በንቃት እንዲሳተፉ እና እንዲሰሩ እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን አብራርተዋል፡፡
ሴት ነጋዴዎች በመደራጀት በሀገር ውስጥና በወጪ ንግድ ስራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ያስሚን ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡበት እድል መፈጠሩንም አስረድተዋል፡፡
ሁንተናዊ ተሳትፏቸውን ለማሳደግ በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ በCOMESA እና በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ እየተሳተፉ ሲሆን ይህም በማንኛውም የሰራ ዘርፍ ቢሰማሩ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡









