በወጪ ንግድ ለተሰማሩ ሴት ነጋዴዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
አዲስ አበባ: መጋቢት 3/2018 ዓ.ም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከትሬድ ማርክ አፍሪካ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በወጪ ንግድ ለተሰማሩ ሴት ነጋዴዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነው።
ስልጠናውን ያስጀመሩት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የንግድ ትስስርና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ያስሚን ውሃብረቢ ባስተላለፉት መልእክት የወጪ ንግዱን በማሳለጥ ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንድታገኝ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።
የገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋፋት ከሀገራት ጋር የሁለትዮሽና ማልቲ ላተራል የንግድ ስምምነቶችን የመፈራረም የአሰራር ማሻሻያዎችን በመተግበር ማነቆዎችን በመፍታት ዘመናዊና ምቹ የንግድ ምህዳር እንዲፈጠር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ ያስሚን ገልፀዋል።
ወ/ሮ ያስሚን እንደገለፁት እየተፈጠሩ ያሉ የገበያ እድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም በህጎችና በንግድ ስምምነቶች እንዲሁም በአማራጭ የወጪ ንግድ የገበያ እድሎች ዙሪያ ለሴት ነጋዴዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የሚላኩ ምርቶ በጥራት፣ በዋጋና በመጠን ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል መድረኩ መመቻቸቱንም አንስተዋል።








