የኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ይድነቃቸው ወርቁ በቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ የሚገነባውን ዘመናዊ የቁም እንሰሳት የግብይት ማዕከል ለማስጀመር ሞያሌ ከተማ ገቡ።
ሚኒስትር ዴኤታው ቦረና ዞን ያቤሉ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በክቡር አቶ አብዱሰላም ዋሪዮ የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ የደመቀ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ከ200 ኪሎ ሜትር የመኪና ጉዞ በኋላ ሞያሌ ከተማ ሲደርሱ በሞያሌ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ገልማ ከሮጲቻ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ስርዓቱን ለሁሉም ተዋናይ አካላት ምቹና ዘመናዊ እንዲሁም የምርት ጥራትንና ተወወዳዳሪነትን ለማሳደግ ዘመናዊ የግብይት ማዕከላትንና ሌሎች የገበያ መሠረተ ልማቶችን በማስገንባትና ማስፋፋት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
ይህ በሞያሌ ወረዳ የሚጀመረው ዘመናዊ የቁም እንሰሳት የግብይት ማዕከል የአካባቢውን እምቅ የቁም እንሰሳት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሚያስችል ይታመናል።











