የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ በጄኔቫ/ሴውዘርላንድ ዛሬ በተጀመረው የአለም ንግድ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ (General Council) ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኒጎዚ ኦኮንጆ ኢዌላ እና የኢትዮጵያ የስራ ቡድን ስብሰባ አምባሳደር ሪብቃ ፊሼር ጋር በኢትዮጵያ የድርጅቱ አባልነት ሂደት ላይ ውይይት ማድረጋቸውንም ገልፀዋል።
በውይይታችንም በኢትዮጵያ በኩል በባለ-ብዙ እና በሁለትዮሽ የድርድር መድረክ ላይ የተከናወኑ አበይት ተግባራት እና ተግዳሮቶች ላይ የመከርን ሲሆን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና የቴክኒክ አቅም ላይ እንደምትገኝ እና የድርድር ሂደቱ በፍሬ-ነገርም ጭምር የላቀ መሆኑን ጠቅሼያለሁ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የድርጅቱን አባልነት ለማሳካት በትኩረት እየሰራች መሆኗን እና ሁለንተናዊ ዝግጁነት እንዳላት ማብራራታቸውን በመጥቀስ ። በተጨማሪም ሂደቱ አሁን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በመድረሱና ድርድሩን ለማጠናቀቅ በሃገራችንም ሆነ በዓለም ንግድ ድርጅት ሴክሬታሪያት በኩል ትኩረት ተሰጥቶት ድጋፍ መስጠት እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ክቡር ሚኒስትሩ ጠቁመዋል ።
የዓለም ንግድ ድርጅ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኒጎዚ ኦኮንጆ እና አምባሳደር ርብቃ ላምፕ በበኩላቸው የኢትዮጵያ አባልነትን በከፍተኛ ትኩረት የሚደግፉ መሆኑን ማረጋገጣቸውንም ገልፀዋል ፡፡




