የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒሰትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ከዩናይትድ ኪንግዶም ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማይክል ዎከር ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር አካህዱ።
ታህሳስ 8/2018ዓ.ም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በዛሬው ዕለት በጄኔቫ በመካሄድ ላይ ከሚገኘው የዓለም ንግድ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከዩናይትድ ኪንግደም ዋና የንግድ ተደራዳሪ ማይክል ዎከር ጋር በበየነ መረብ ውጤታማ የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድር ማድረጋቸውን ገለፁ።
በሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድሩ ስምምነት ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያ የሚጠበቅባትን ርቀት እየተጓዘች መሆኑን እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ ከሌሎች አባል ሀገራት የሚነሱ ጥያቄዎችን የሃገርን ብሄራዊ ጥቅም ታሳቢ ባደረገ መልኩ በአዎንታ ተቀብላ ምላሽ እየሰጠች እንደምተገኝ ክቡር ሚኒስትሩ አንስተዋል ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ዩኬ በባለብዙ ወገን ድርድሮች ለኢትዮጵያ እያደረገች ላለው ድጋፍና በስራ ቡድን ስብሰባ ሊቀመንበርነት ሚናዋ ለሰጠችው ውጤታማ አመራር ምስጋና አቅርበዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም የንግድ ዋና ተደራዳሪ ማይክል ዎከር በበኩላቸው ዩናይትድ ኪንግደም የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድሩን ለማሳለጥና ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን እንድትቀላቀል ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ያረጋገጡ መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።



