የንግድ ዘርፍ ስኬት
Back

የንግድ ዘርፍ ስኬት

Motri
5 min read

በበጀት ዓመቱ ባለፋት 6 ወራት በንግድ ዘርፉ የላቀ ውጤት ተመዝግቧል። ክቡር አቶ እንዳለው መኮንን

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይት መድረኩ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጥራት መሠረተ ልማትና ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ እንዳለው መኮንን የተቋሙን የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በግማሽ በጀት ዓመቱ በሁሉም የንግድ ዘርፍ በላቀ አፈፃፀም በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

ለአብነትም በግማሽ በጀት ዓመቱ በወጪ ንግድ ተችሏል ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማስገኘት ታቅዶ 5.1 ቢሊዮን ዶላር ወይም የእቅዱን 120% መፈፀሙን፣ ለ1,862,826 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦንላይን ለመስጠት ታቅዶ 2,305,327 አገልግሎቶች መሰጠቱን ወይም የእቅዱን 124% መፈፀሙን ገልፀዋል አቶ እንዳለው።

የድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽንና ሪጉላቶሪ ሽፋንን ለማሳደግ በግማሽ ዓመቱ በ953,662 ድርፐጅቶችን ኢንስፔክት ለማድረግ ታቅዶ በ1,002181ላይ ወይም የእቅዱን 105% መፈፀሙን ገልፀዋል።

የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ግሽፈትን ለመቀነስ በተሰራው ከፍተኛ ስራ የዋጋ ግሽፈት ወደ ነጠላ አሃዝ (9.7%) ማውረድ ተችሏል።

የገቢና የወጪ እንዲሁም የፋብሪካ ምርቶችን ጥራት የማረጋገጥና የኢ- ኮመርስ ንግድን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ለመምራት የተሰሩ ስራዎችና የተገኘው ውጤት የላቀ መሆኑን አቶ እንዳለው በሪፖርታቸው አቅርበዋል።

ጥር 21 ቀን 2018ዓ.ም

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#Motri#coffee