የንግድ ሚኒስቴር ግምገማ
Back

የንግድ ሚኒስቴር ግምገማ

Motri
5 min read

የኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች “ጥንካሬያችን በአንድነታችን፣ ስኬታችን በጋራ ጥረታችን፤ ለላቀ ውጤትና ለንግድ ሥነ-ምህዳር መዘመን” በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸምና የንግድ ዘርፍ የመንግሥት አስተዳደር ሪፎርም ያለበትን ደረጃ የሚዳስስ ሪፖርት ላይ ገንቢ ውይይት አድርገዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት የንግድ ዘርፉን ወደሚጠበቅበት ከፍታ ለማድረስና የሀገራችንን የብልጽግና ራዕይ ለማረጋገጥ በሚያስችል ቁመና ላይ መሆናቸው በውይይቱ ተመላክቷል።

በተለይም በ118 ዓመት የተቋሙ ታሪክ ውስጥ ዘመኑን የዋጀ የንግድ ፖሊሲን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የመጨረሻ ምዕራፍ ሥራ መከናወኑ የሪፎርሙ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል።

ክቡር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ባለፉት ወራት በመሰጠት፣ በመቀናጀትና በማላቅ እሴቶች ተመርቶ አመርቂ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን፤ በቀጣይም የሪፎርም ትግበራውን በብቃት በማከናወን ሁለንተናዊ ተቋማዊ ለውጥን ለማሳካት የጋራ አቋም ተይዟል።

በመደመር መንግሥት የትብብር ሞዴል ኢንተርፕሪነር በሆነ ዕሳቤ የግሉን ዘርፍ በመደገፍ፣ የንግድ ዕድገትን የሚገድቡ ሳንካዎችን በመለየትና በመፍታት ፍትሐዊና አካታች የንግድ ሥነ-ምህዳር እንዲፈጠር በትጋት መሥራት እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ይህ መድረክ የተቋሙን የመከወን አቅም በማሳደግ፣ አዳዲስ ሐሳቦችን በማመንጨትና እሴት በመጨመር ለላቀ ውጤት በጋራ ለመቆም ቃል የተገባበት ሆኖ ተጠናቋል።

“ዘመናዊ የንግድ ሥነ-ምህዳር ለሀገር ብልጽግና!”

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9

Tags

#Motri#coffee