የነዳጅ ዋጋ እና የዋጋ ግሽበት
Back

የነዳጅ ዋጋ እና የዋጋ ግሽበት

Motri
5 min read

በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር በጣም ዝቅተኛ ነው። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ: ጥር 26/2018 ዓ.ም በአለም ላይ የነዳጅ ዋጋ በየጊዜው እንደሚቀያየርና በኢትዮጵያ የነዳ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) አስታወቁ።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ አሁን ላይ በአለም በተለያዩ ምክንያቶች የነዳጅ ዋጋ እንደሚቀያየርና ሀገራትም የነዳጅ ዋጋን በየቀኑ እንደሚከልሱ ገልፀው በኛ ሁኔታ ባለፈው በጀት ዓመት የነዳጅ ዋጋ የከለስነው 7 ጊዜ ብቻ ነው ብለዋል።

የነዳጅ ዋጋን ከቅርብ ጎረቤት ሀገራት ጋር ሲናነጻጽር በጅቡቲ ህጋዊ ዋጋ 297 ብር፣ በኬኒያ 220 ብር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ 129 ብር ነዉ፡፡ ይህ ደግሞ መንግሥት ወደብ ካላቸዉ ሀገራት ባነሰ ዋጋ ነዳጅን በድጎማ እያቀረበ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል ብለዋል፡፡

ይሄም ሆኖ ነዳጅን ለመቅዳት በየቦታዉ ሰልፎችን መቀነስ ላይ ችግሮች እንደሚስተዋሉ ያነሱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለዚህ ችግር መፍትሔ ለማበጀት በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የዋጋ ግሽፈት ወደ 9.7%(ነጠላ አሃዝ) ማውረድ ተችሏል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ: ጥር 26/2018 ዓ.ም የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽፈት ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳይፈጥር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ በሰራው ስራ የዋጋ ግሽፈትን ወደ ነጠላ አሃዝ(9.7%) ማውረድ መቻሉን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) ገለፁ።

የቅርቦትና ፍላጎትን ለማመጣጠን በተሰራው ስራና ለመንግስት ሰራተኞችና ጡረተኞች የተደረገው የደሞዝ ጭማሪ፣ በነዳጅ ማዳበሪያና በሌሎች ምርቶች ላይ የተደረገው ድጎማ በግብይት ስርዓቱ ላይ የሚደረገው ቁጥጥር ፣ አማራጭ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችና ትላልቅ ዘመናዊ የግብይት ማእከላት ተገንብተው ወደ ስራ መግባት ገበያው እንዲረጋጋና ግሽፈቱ እንዲቀንስ አድርጎታል ብለዋል።

በተጨማሪም ውጤታማ የበጀት አስተዳደር በተለይም መንግስት ከብሄራዊ ባንክ ብድር አለመውሰዱና ዘመን ገበያን የመሳሰሉ የቨርቹዋል ግብይትም ለግሽፈቱ መቀነስ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2

Tags

#Motri#coffee