የምርት ጥራት ቁጥጥር እየተጠናከረ ነው
Back

የምርት ጥራት ቁጥጥር እየተጠናከረ ነው

Motri
5 min read

በወጪና ገቢ ምርቶች እንዲሁም የፋብሪካና የገበያ ምርቶች ጥራት ቁጥጥር ስራ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 26/2018 ዓ.ም በወጪና ገቢ ምርቶች እንዲሁም በፋብሪካና በገበያ ምርቶች ላይ የሚደረገው የጥራት ቁጥጥር ስራ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ባለፉት 8 ወራት በ39 አይነት የገበያ ምርቶች ላይ የጥራት ቁጥጥር ለማድረግ አቅዶ በ41 አይነት የገበያ ምርቶች ላይ ቁጥጥርና ፍተሻ በማድረግ የእቅዱን 105 በመቶ ፈጽሟል፡፡

በዚህም በ41 የምርት አይነቶች ላይ 169 ወካይ ናሙናዎችን በመውሰድ ባደረገው የጥራት ፍተሻ መሰረት 91 ወካይ ናሙናዎች የተቀመጠውን የጥራት መስፈርት ያላሟሉ 78 ወካይ ናሙናዎች ደግሞ የተቀመጠውን የጥራት መስፈርት ያሟሉ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በ1,252,285 ሜትሪክ ቶን የገቢ ምርቶች ላይ የጥራት ቁጥጥርና ፍተሸ ለማድረግ አቅዶ በ2,322,960 ሜትሪክ ቶን የገቢ ምርቶች ላይ ቁጥጥርና ፍተሸ ማድረጉንና ከዚህ ውስጥ 114.16 ሜትሪክ ቶን የገቢ ምርቶች ከደረጃ በታች መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማገዱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል በ360 ፋብሪካዎች ላይ የጥራት ቁጥጥር ለማድረግ አቅዶ በ346 ፋብሪካዎች ላይ ቁጥጥር በማድረግ የእቅዱን 96.1% ተፈጽሟል። በዚህም ከ183 ፋብሪካዎች ላይ 248 ወካይ ናሙና በመውሰድ ባደረገው የጥራት ፍተሸ  58 ወካይ ናሙናዎች የጠቀመጠውን የጥራት መስፈርት ያላሟሉ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በተደረገው የጥራት ፍተሸ መሰረት ከደረጃ በታችና የጥራት ጉድለት በተገኘባቸው የፋብሪካና የገበያ ምርቶች ላይ ጥራታቸው እስኪረጋገጥ ድረስ ለገበያ እንዳይቀርቡ ማገድን ጨምሮ ምርቶቹ እንዲወገዱ የማድረግ እርምጃዎችን የወሰደ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

Gallery

Gallery image 1

Tags

#Motri#coffee