የሞያሌ ቢቃ የከብት ገበያ ግንባታ ተጀመረ
Back

የሞያሌ ቢቃ የከብት ገበያ ግንባታ ተጀመረ

Motri
5 min read

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ይድነቃቸው ወርቁ በኦሮምያ ክልል ቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ ቢቃ ቀበሌ የሚገነባውን ሞያሌ ቢቃ 2ኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታን በዛሬው እለት በይፋ አስጀመሩ።

የ ሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ ይድነቃቸው ወርቁ በቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ ቢቃ ቀበሌ በአለም ባንክ ድጋፍ ድራይቭ ፕሮጀክት የሚገነባውን ሞያሌ ቢቃ 2ኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል የመሠረት ድንጋይ በማኖር የግንባታ ሥራውን በይፋ አስጀምረዋል።

ክቡር አቶ ይድነቃቸው በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የንግድ ስርዓቱን ለሁሉም ተዋናይ አካላት ምቹና ዘመናዊ እንዲሁም የምርት ጥራትንና ተወወዳዳሪነትን ለማሳደግ ዘመናዊ የግብይት ማዕከላትንና ሌሎች ሰፋፊ የገበያ መሠረተ ልማቶችን በማስገንባትና በማስፋፋት ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ይህ በሞያሌ ወረዳ የሚጀመረው ዘመናዊ የቁም እንሰሳት የግብይት ማዕከል የአካባቢውን እምቅ የቁም እንሰሳት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ በማዋልና አርብቶ አደሩ ከቁም እንሰሳቱ ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ከማስቻሉም ባሻገር ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን የወጪ ንግድ ገቢ ያሳድገዋል ተብሎ ይታመናል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በትናንትናው እለት በደቡብ ኦሞ ዞን የቀይ አፈር 2ኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታን በይፋ ማስጀመራቸው ይተወሳል።

እነዚህ ግንባታዎች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የገበያ መሠረተ ልማት ስብራትን ለመጠገንና የንግድ ሥነ-ምህዳሩን እስከ

ታችኛው መዋቅር ድረስ ለማዘመን የጀመረው የስትራቴጂካዊ ጉዞ አካል ናቸው።

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9
Gallery image 10

Tags

#Motri#coffee