የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር  ሪፎርም ትልልቅ የመንግስትና የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ያለመ ነው። ዶ/ር አብዱልሃኪም ሙሉ
Back

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትልልቅ የመንግስትና የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ያለመ ነው። ዶ/ር አብዱልሃኪም ሙሉ

Motri
5 min read

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትልልቅ የመንግስትና የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት ያለመ ነው። ዶ/ር አብዱልሃኪም ሙሉ

=============

ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሰራተኞች በንግድ ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ላይ በዛሬው እለት ተወያይተዋል።

መድረኩን ያስጀመሩት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር አብዱልሃኪም ሙሉ እንዳሉት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትልልቅ የመንግስትና የህዝብ ፍላጎትን ለማሟላት ያለመ መሆኑን አንስተው በተለይም ዘመናዊነትን የተላበሰ፣ ብቃትና ጥራት ያለው አገልግሎትን ለህዝብ ለመስጠት፣ ፍትሃዊ ግልፅና ገለልተኛ ተቋም ለመፍጠርና በዚህም የህዝብን እርካታ ለማምጣት መሆኑን ገልፀዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘው ሪፎርሙ የመንግስትን የማስፈፀም አቅም በእጅጉ እንደሚያሳድግ የሰራተኛውን ብቃትና ተነሳሽነት እንደሚጨምር እንዲሁም የተገልጋዮችን እርካታ ማጎናፀፍ የሚያስችል አገልግሎት መሥጠትን ያሳድጋል ብለዋል።

ከሪፎርሙ ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ስጋትና ጥርጣሬዎችን ለማጥራትና ግልፅነትን ለመፍጠር የውይይት መድረኩ ጠቃሚ መሆኑን አንስተው ሰራተኛው የንግድ ዘርፉን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ላይ የጠራ ግንዛቤ በመያዝ ለሪፎርሙ ስኬት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የንግድ ዘርፍ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታን ለውይይት ያቀረቡት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሥራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳሙኤል አለነ ሲሆኑ ከተሳታፊዎቹ ጥያቄና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶበታል።

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7

Tags

#Motri#coffee