የኢትዮጵያ ደረጃዎች ቦርድ ስብሰባ
Back

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ቦርድ ስብሰባ

Motri
5 min read

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ቦርድ 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂደ።

​ቦርዱ የሀገራችንን የንግድ ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጡ፣ የገበያ ሥርዓቱን የሚያዘምኑና ለኢኮኖሚ ዕድገታችን ፋይዳ ያላቸው ቁልፍ ብሔራዊ አስገዳጅ ደረጃዎች መርምሮ አጽድቋል።

እነዚህ የጸደቁት ደረጃዎች በዋናነት በምግብና እርሻ፣ በኢንዱስትሪ፣ በኤሌክትሮሜካኒካል፣ በሳይበር ደህንነት፣ በንግድ መሠረተ ልማት እና በጂኦግራፊያዊ መረጃ ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ናቸዉ።

የቦርዱ ሰብሳቢና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በስብሰባው ላይ እንደገለጹት፤ ​የእነዚህ ደረጃዎች መጽደቅ ለሀገራችን የጥራት መሠረተ ልማት ዕድገት ትልቅ ፋይዳ አለው።

ይህም አምራቾችና አገልግሎት ሰጪዎች የጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑ ገልጸዋል።

ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ምርትና አገልግሎት ለሀገር ዕድገት መሠረት መሆኑን በመገንዘብም፤ የጸደቁት ደረጃዎች ወጥነት ባለው መልኩ ወደ ተግባር እንዲገቡ ተቆጣጣሪ ተቋማት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትሩ ጥብቅ መመሪያ ሰጥተዋል።

​በመጨረሻም ለደረጃዎቹ ተፈጻሚነት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ክቡር ሚኒስትሩ በስብሰባው ላይ አረጋግጠዋል።

​ጥራት ለተወዳዳሪነት!

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9
Gallery image 10

Tags

#Motri#coffee