የሁለተኛው ዙር የቡና ግብይትና ኤክስፖርት ዶክመንቴሽን ሰልጣኞች የመስክ የተግባር ስልጠና ልምምዳቸውን ገለፃ አደረጉ፡፡
Back

የሁለተኛው ዙር የቡና ግብይትና ኤክስፖርት ዶክመንቴሽን ሰልጣኞች የመስክ የተግባር ስልጠና ልምምዳቸውን ገለፃ አደረጉ፡፡

ECTA
5 min read

የሁለተኛው ዙር የቡና ግብይትና ኤክስፖርት ዶክመንቴሽን ሰልጣኞች የመስክ የተግባር ስልጠና ልምምዳቸውን ገለፃ አደረጉ፡፡

(ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም፡ኢ/ቡ/ሻ/ባ)

አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቡና ማሰልጠኛ ማዕከል የሚሰለጥኑ ሀያ አራት(24) የሁለተኛው ዙር የቡና ግብይትና ኤክስፖርት ዶክመንቴሽን ሰልጣኞች በተመረጡ የቡና ኤክስፖርተሮች በአካል በመሄድ የተግባር የልምድ ልውውጥ ስልጠና ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

ሰልጣኞቹ በአምስት የሀገሪቱ ታዋቂ የቡና ኤክስፖርተሮች በሆኑት በአርደንት፣ስናፕ፣ሜታድ፣ቢ.ኤን.ቲ እና ለገሠ ሸረፋ በተባሉ ቡና ላኪዎች ተቋም በመሄድ የልምድ ልውውጥ ያደረጉ ሲሆን የቡና ላኪ ባለቤቶችና አመራሮችም በገለፃው ወቅት ተገኝተው የሰልጣኞችን ጥረትና መነሳሳት አመስገነዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የገበያ ልማትና ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ እና የባለስልጣን መ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ዑመር እንደገለፁት የቡናን ምርትና ምርታማነትን በመጨመር በጥራት በማምረት እና በቴክኖሎጂ በመታገዝ በዘመናዊ የግብይት ዘዴ ቡናን ወደላቀና ከፍ ወዳለ ደረጃ አድርጎ መስራት ይጠበቃል፡፡ ይህ የቡና ማሰልጠኛ ማዕከልም በዕውቀት የታገዘ ስራ እንዲሰራ በማሰልጠን ላይ የሚገኝ እና በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው በማድረግ እየተሰራበት ይገኛል ብለዋል፡፡ አቶ ሻፊ አክለውም ቡናን እናሳድጋለን ካልን ቡናን በዕውቀት መስራት ይጠይቃል፡፡ ይህ ከሆነ ሴክተሩ ወደኋላ እንዳይቀር ይረዳል ብለዋል፡፡ ስለሆነም ይህ የተግባር ላይ የልምድ ልውውጥ በማዕከሉ የሚወጡትን ሰልጣኞች ከማብቃትና ተገቢውን ዕውቀትና ልምድ በማግኘት ረገድ ፋይዳው የላቀ ስለመሆኑ እምነታቸውን ገልፀው መድረኩን በይፋ ከፍተዋል፡፡

የባለስልጣን መ/ቤቱ የዋና ዳይሬክተር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰፊሳ አባቡ በበኩላቸው ሴክተሩ ትልቅ ሀብት የሚዘዋወርበት ቢሆንም በዘርፉ በቂ የሚባል የሰው ኃይል እንደሚያስፈልገው በመገንዘብ የባለስልጣን መ/ቤቱ ይህን የመሰለ የቡና ማሰልጠኛ ማዕከል ገንብቶ በርካታ ሰልጣኞችን በተለያየ ዙር በማሰልጠን በዘርፉ ያለውን የባለሙያ ክፍተት እየሞላ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ማዕከል መሰልጠናችሁን እንደ ትልቅ ዕድል በመውሰድ ወደፊት በብቃትና በታማኝነት ሀገራችሁን እንደትጠቅሙ በማለት ከአደራ ጭምር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመቀጠልም በአምስት ቡድን የተከፋፈሉት ሰልጣኞች ከመስክ የተግባር ስልጠኛው ያገኙትን ዕውቀትና ልምድ ገለፃ አድርገው በተነሱ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ማዕከሉን ከምስረታው ጀምሮ ድጋፍ የሚያደርገው የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(UNIDO) ኃላፋዎችና አስተባባሪዎች በመድረኩ መገኘታቸው ታውቋል፡፡

ዘገባው የተስፉ አለማዬሁ ነው፡፡

(ኢ/ቡ/ሻ/ባ)

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7

Tags

#ecta#coffee