የቡና ትርጉም ማዕከል ተመረቀ
Back

የቡና ትርጉም ማዕከል ተመረቀ

ECTA
5 min read

የቡና መማማሪያ ማዕከል (COFFEE INTERPRETATION CENTER /CIC/) የምረቃ መርሀ ግብር ተካሄደ

የካቲት 06/2018 ዓ.ም

ኢቡሻባ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከስፓኒሽ ኮኦፖሬሽን ጋር በመተባበር የገነባውን የቡና መማማሪያ ማዕከል (COFFEE INTERPRETATION CENTER/CIC/) አስመርቆ በይፋ ስራ አስጀመረ።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የተከበሩ ዶ/ር አዱኛ ደበላ ከምክትላቸው ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር እና ከስፓኒሽ ኮኦፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ማዕከሉን መርቀው ከፍተዋል። በምረቃ መርሀ ግብሩም የOSSREA እና የWOMEN IN COFFEE የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በምረቃውም ወቅት የተዘጋጀውን የማዕከሉን ውስጣዊ አደረጃጀት የተመለከቱ ሲሆን በእያንዳንዱ ዲስፕሌይ ላይ የተመለከተውን የቡና ገጽታ ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

በግምባታው ሂደት OSSREA እና WOMEN IN COFFEE የተሰኙ ድርጅቶች ጥናት በማካሄድና ለማዕከሉ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሰባሰብ ቁልፍ ሚና እንደተጫወቱ ተገልጿል።

ማዕከሉ በይዘት ደረጃ ቡና ከዘር እስከ ኤክስፖርት ምን እንደሚመስል እውቀትና ክህሎት ማስጨበጫ ማዕከል እንደሚሆንና የቡና ታሪክ፣ የሴቶች ሚና በቡናው ዘርፍ፣ ቡና ለኢኮኖሚና ማኅበራዊ ሕይወት ያሉት ጠቀሜታዎችንና ሌሎች ይዘቶችንም ያካተተ እንደሆነ ተብራርቷል። በዚህም የቡናን ሁለንተናዊ ጉዳይ ለዓለም የሚተዋወቅበት ማዕከል እንሚሆን ነው የተወሳው።

ይህ የመጀመሪያው ደረጃ ( 1st Phase) ሂደት እነደሆነና በቀጣይ በሁለተኛው ዙር (2nd phase) ግንባታ ዲጂታላይዝድ እንደሚሆን ተወስቷል።

ሁለቱንም የማዕከሉን የማደራጀት ምዕራፍ በሀላፊነት ወስዶ እየሰራ ያለው አብላዝ ላብ (Ablaze Lab.) የተሰኘ አገር በቀል ድርጅት እንደሆነ ተገልጿል።

የድርጅቱ መስራችና ባለቤት ላደረግንላቸው ቃለ መጠይቅ ማብራሪያ ሲሰጡም ዲጂታላይዝ በማድረጉ ሂደት ስለሚከናወኑ ተግባራት ሲገልጹ ሁለት ሶፍትዌሮችና አፕልኬሽኖች  እንደሚበለጽጉ በእነዚህም አኒሜሽን የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎች ማዕከሉን ለማዘመን ጠቀሜታ ላይ እንደሚውሉ ገልጸው በቪዲዮና በኦዲዮ ( በምስልና በድምጽ) የታገዘ ማዕከል እንደሚሆን ታውቋል።

ከቀናት በፊት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ከጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት የተለያዮ የቡና ማዕከላትን በመገንባት የኢትዮጵያ ቡናን የማሳደግ ስራ ባለስልጣን መስሪያቤቱ እየሰራ እንደሆነ መዘገባችን ይታወሳል።

አሸናፊ ጌታሁን ዘግቦታል

Tags

#ECTA#coffee