የቡና ጣዕም በሳይንስ ሚዛን
Back

የቡና ጣዕም በሳይንስ ሚዛን

ECTA
5 min read

ይህ ካፌዎችን፣ የቡና ቆዪዎችንና በቤታቸው ቡና የሚያፈሉ ሰዎችን ልማድ ሊቀይር የሚችል ግኝት በኬሚስትሪ ምሁሩ ክሪስቶፈር ሄንደን በሚመራ ቡድን ይፋ ሆኗል።

ተመራማሪዎቹ እንደገለጹት፤ በአንድ ስኒ ቡና ውስጥ የኤሌክትሪክ ፍሰት (Current) በማሳለፍ የቡናውን ጣዕም በሞለኪውል ደረጃ በከፍተኛ ጥንቃቄ መለካት ይቻላል።

​ለዚህ ተግባር ተመራማሪዎቹ የተጠቀሙት "ፖቴንሺዮስታት" (Potentiostat) የተባለና አብዛኛውን ጊዜ ለባትሪና ለነዳጅ ሴል (Fuel cell) ምርመራ የሚያገለግል የላቦራቶሪ መሣሪያን ነው።

መሣሪያው የቡናውን ልዩ "የኬሚካል አሻራ" (Chemical fingerprint) መለየት የሚችል ሲሆን፤ ይህ አሻራ የቡናውን ጥንካሬና የቁሌቱን መጠን (Roastiness) በዝርዝር ያሳያል። እነዚህ ሁለት መለኪያዎች ደግሞ ማንኛውም ሰው ቡና ሲጠጣ የሚሰማውን እውነተኛ ጣዕም የሚወስኑ ቁልፍ ነገሮች ናቸው።

​ለምን ይህ ዜና ትልቅ ትርጉም ኖረው?

​ወጥነት ያለው ጣዕም፦ የቡና ቆዪዎችና ባሬስታዎች ሁልጊዜ አንድ ዓይነት ጥራት ያለው ቡና እንዲያቀርቡ ይረዳቸዋል።

​ሳይንስና ጥበብ፦ የቡና አፈላልን ከባሕላዊ ልምድ ባለፈ ወደ ተረጋገጠ ሳይንሳዊ መረጃ ያሸጋግረዋል።

​ቴክኖሎጂው፦ ቀደም ሲል ለኃይል ማመንጫ ምርምር ይውል የነበረ መሣሪያ አሁን ለጠዋት ቡናችን ጥራት መጠበቂያ መዋሉ አስገራሚ ነው።

አንድ ስኒ ቡና ውስጥ በመጨረሻ የምንጠብቃት ጣዕም በብዙ ሚስጥራዊና ረቂቅ ሁኔታዎች የተከበበች ናት፤ የውኃው ሙቀት፣ የዱቄቱ መድቀቅ እና መሸርከት፣ የቡናው ዝርያና የተገኘበት አካባቢ፣ የቁሌቱ ደረጃ እንዲሁም የማፍያ ሰዓቱ ጥቂቶቹ ናቸው። በእነዚህ ልኬቶች ላይ የሚደረግ ቅንጣት ታክል ለውጥ፣ ወደ ሲኒው የሚቀዳውን የቡና ጣዕም ሙሉ በሙሉ ሊቀይረው ይችላል። በመሆኑም ጥራት ላይ ትኩረት ለሚያደርጉ ካፌዎች እና ለተመረጡ ደንበኞቻቸው፣ የቡናን ወጥ ጣዕም ጠብቆ ማቆየት ሁልጊዜም በልምድና በትንንሽ ማስተካከያዎች የሚደረግ አድካሚ ትግል ነው።

​በኦሪገን ዩኒቨርሲቲ የተገኘው ይህ የኤሌክትሮ-ኬሚካል ስልት ግን፣ ለዚህ ፈተና ጥልቅና የተራቀቀ መፍትሔ ይዟል። "ፖቴንሺዮስታት" መሣሪያው ቡናው ለተለካ የኤሌክትሪክ ቮልቴጅና ፍሰት የሚሰጠውን ምላሽ በመመርመር፣ ሊደረስባቸው የማይችሉ ረቂቅ የኬሚካል ልዩነቶችን በግልጽ ያሳያል።

​ባጭሩ፦ ይህ ግኝት የቡናን ጥበብ በሳይንስ ሚዛን በመለካት፣ ግምትና ጥርጣሬ የሌለበትን ፍጹም ጣዕም ለማግኘት መንገድ ከፍቷል።

መረጃውን ያገኘሁት  ከ Coffee Geography Magazine) ሲሆን ፀሀፊው

ዲ. ኤል. ገመዳ ናቸው።

Tags

#ECTA#coffee