የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የማሳ መረጃ በትክክል መሰብሰብና መያዝ ወሳኝ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ገለፀ
ሆሳዕና 24/04/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ቅመማ ቅመም ባላስልጣን ጋር በመተባበር በኢዩ-ካፌ በጀት ድጋፍ በEUDR ህጎችና የአርሶአደሮች ቡና ማሳ መረጃ አሰባሰብ ዙሪያ ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሶምሶን ወ/ግዮርግስ በበኩላቸው ስልጠናው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ቅመማ ቅመም ባላስልጣን ጋር በመተባበር በኢዩ-ካፌ በጀት ድጋፍ በEUDR ህጎችና የአርሶአደሮች ቡና ማሳ መረጃ አሰባሰብ ዙሪያ እየተሰጠ ነው ብለዋል ።
ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የሆነ እና የምርቱ መነሻና ወቅቱ የተረጋገጠ እንድሁም የተሻለ ግብይት እንድካሄድ የሚያስችል ስልጠና እንደሆነም ተናግረዋል ።
የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የማሳ መረጃ በትክክል መሰብሰብና መያዝ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል ።
የሁሉም አርሶአደሮች ከተከለ እስከ ምርት አሰባሰብ ድረስ ያለውን የቡና መረጃ ለመሰባሰብ የጋራ ግንዛቤ እንድኖር ነው ብለዋል ።
በቡና ልማት በቴክኖሎጂ የተደገፈ መረጃ በመያዝ የግብይት ሂደቱን በማሳለጥ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ የስልጣናው ፋይዳ የጎላ እንደሆነም አንስተዋል ።
የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ሀብታሙ ታደሰ በስልጠና ወቅት እንደገለፁት ስልጠናው በቡና ምርት ግብይት ፣በመረጃ አሰባሰብና በጥራትና በአመራረት ዘይቤ ትኩረት ያደርጋል ።
የቡና ምርት አያያዝን በቴክኖሎጂ ከማስደገፍ አንጻር የሚስተዋሉ ውስንናቶችን ለማስቀረት በሚል በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ዶክተር ሀብታሙ ተናግረዋል ።
በየአከባቢው የሚገኙ የቡና አምራቾችና የማሳ ሽፋን ተለይቶ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ልዩ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸውም አንስተዋል ።
ሰልጣኞች እየተሰጠ ያለውን ትምህርትና ስልጠና በአግባቡ በመከታተል በየአካባቢያቸው የአርሶአደሮችን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ የድርሻቸውን እንድወጡም አስገንዝበዋል ።
የሀድያ ዞን ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተማም ስርጎታ እንደተናገሩት በዞኑ ከዚህ ቀደም የቡና ሽፋን 20 ሺህ ሄክተር ከነበረበት በተያየዘው በጀት ዓመት ወደ 42 ሺህ ሄክተር ማሳደግ ተችሏል ።
የጉራጌ ዞን ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት የኃላፊ ተወካይ አቶ ታሪኩ ወርቁ በዞኑ የቡና ሽፋን 55 ሺህ ሄክተር እንደሆነ ገልጸው ይህ ስልጣና ህገወጥ ተግባራትን በመከላከል አምራቹ በቀጥታ ከገዥ ጋር እንድገነኝ እድል ይፈጥራልም ብለዋል ።
ከዚህ ቀደም የቡና ምርትን በተለምዶ በማምረት በአከባቢው ገበያ በማቅረብ የተጠቀሚነት ጉድለት እንደነበር ያነሱት ሀላፊዎቹ ከሽፋን ባለፈ ጥሩ ምርት የሚሰጥና በሽታን መቋቋም የሚችል የቡና ዝርያዎችን ተደራሽ በማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ።
የአርሶአደሮችን ተጠቀምነት ለማረጋገጥ በገበያ ትስስር ዙርያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል ።
ምንጭ ሀድያ ቴሌቪዥን








