የቡና ኤክስፖርት ዕድገት
Back

የቡና ኤክስፖርት ዕድገት

ECTA
5 min read

የመንግስት ሁለንተናዊ ድጋፎች የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ያለውን ተወዳዳሪነት እያሳደገው ነው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2018

መንግስት ለቡናው ዘርፍ እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ ያለውን ተወዳዳሪነትና ተመራጭነት በከፍተኛ ደረጃ እንዳሳደገው የዘርፉ ላኪዎች ገለጹ።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ተፈላጊነት እየጨመረ ከመምጣቱ በላይ አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎች እየጨመሩ ይገኛሉ።

ይህንን ተከትሎም ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘው የውጭ ምንዛሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት እያሳየ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት 469 ሺህ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ በመላክ 2 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘት ችላለች።

ይህም በሀገሪቱ የቡና ታሪክ ከፍተኛው የገቢ መጠንና የጥራት ደረጃ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ መንግስት ይህንን ውጤት በማስቀጠል በያዝነው ዓመት የሚገኘውን ገቢ ወደ ሦስት ቢሊየን ዶላር ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የቡና ላኪዎች እንደገለጹት፤ በቡናው ዘርፍ እየመጣ ላለው ዕድገትና ስኬት የመንግስት ድጋፍ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የታደሰ ደስታ ስፔሻላይዝድ ኮፊ ኤክስፖርት ዳይሬክተር ገብረመስቀል ሃይሉ እንዳሉት፤ መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ልዩ ትኩረት የኢትዮጵያ ቡና ከአውሮፓ፣ አሜሪካና ቻይና አልፎ በሁሉም የዓለም ክፍሎች ተፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል።

ኢዜአ

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5

Tags

#ECTA#coffee