የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር
Back

የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር

Motri
5 min read

ክቡር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከአምባሳደሮች ጋር የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድርን ለማፋጠን ተወያዩ።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባልነት ድርድር ሂደት ዙሪያ በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጋር ፍሬያማ የቨርቹዋል ውይይት አድርገዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት በተለይ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድርን በማከናወን ላይ በሚገኙ ሀገራት ያሉ አምባሳደሮች፣ ሂደቱን ከማፋጠን አንጻር የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡና በቅንጅት መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከሰባት ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ስምምነትን ስታጠናቅቅ በየሀገራቱ የሚገኙ አምባሳደሮች የነበራቸውን አዎንታዊ አስተዋጽኦ ለቀሪ ድርድሮች እንደ መልካም ተሞክሮ መጠቀም እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

በዚሁ አግባብ በሂደት ላይ ያሉ የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድሮችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ክቡር ሚኒስትሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድሮች ውጤታማነት ለባለብዙ ወገን ድርድሮች ስኬት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በተለይ ሚያዚያ 14 እና 15 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን 7ኛውን የሥራ ቡድን (Working Party) ስብሰባ የኢትዮጵያ አቅም ጎልቶ በሚታይበት የብቃት ደረጃ በማከናወን፣ አባልነቱን እ.ኤ.አ በ2026 ለማጠናቀቅ የሚደረገው ርብርብና ትጋት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ክቡር ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

Ethiopian Ministry of Trade and Regional Integration

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9

Tags

#Motri#coffee