የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ
Back

የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ

Motri
5 min read

“የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መፍታትና ብልሹ አሠራርን ማስወገድ ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል” - ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

(አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም) — የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት የሴክተር አፈጻጸም ግምገማ ጥልቅ ውይይት ተደርጎበት ተጠናቋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት በቀጣይ ጊዜያት ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ጠንከር ያለ የሥራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ሚኒስትሩ በግምገማ መድረኩ እንደገለጹት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና የታዩ ጉድለቶችን ለማረም ተቋማዊ ሪፎርምን ማቀላጠፍና የሥራ ባህልን ማሻሻል ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል።

በተለይም ብልሹ አሠራርንና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በቁርጠኝነት በመፍታት ተቋማቱ ለዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

የቀጣይ ሥራዎችን አቅጣጫ በተመለከተም የወጪ ንግድን በልዩ ትኩረት መከታተል፣ የታቀደ የወጪ ንግድ ማስተዋወቅ ሥራ መሥራት፣ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠናን (AfCFTA) ደረጃ በደረጃ የትግበራ መመሪያ ማዘጋጀትና በዓለም ንግድ ድርጅት የሁለትዮሽ ድርድሮችን ማጠናከር እንደሚገባ

ከዚህም በተጨማሪ የኢ-ኮሜርስ ሥርዓታዊና ይፋዊ ትግበራን ማስጀመር፣ የመጋዘን ደረሰኝ አገልግሎትንና የጠረፍ ንግድን በቅርበት መከታተል የንግድ ሥርዓቱን ለማዘመን ወሳኝ መሆናቸው ተመልክቷል።

በጥራት ቁጥጥር ረገድም የኢንስፔክሽን ሥራዎችን እስከ ክልል በማውረድ በዲሲፕሊን መተግበር፣ የአስገዳጅ ደረጃዎች አተገባበርን በጥናት መለየትና ሀገራዊ የጥራት መሠረተ ልማት አቅምን ለዜጎች በሰፊው ማስተዋወቅ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

በነዳጅና ኢነርጂ ዘርፍም በነዳጅ ግብይት ላይ ያለውን ሞኖፖሊ ማስቀረት፣ ሕገ-ወጥነትና ኮንትሮባንድን መከላከል እንዲሁም በቁጠባ ላይ የተመሰረተ የኃይል አጠቃቀምን መከተል በቀጣይ በልዩ ትኩረት የሚሰሩ ተግባራት መሆናቸው ተገልጿል።

ክቡር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማጠቃለያቸው የመረጃ ትክክለኛነትን በማጥራት የሐሰት ሪፖርቶችን ማስቀረትና የአካባቢ ገበያዎችን ደረጃ ማሻሻል የሴክተሩ አመራሮችና ሠራተኞች ዋና የቤት ሥራ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ በየሴክተሩ ትኩረት ሊደረግባቸዉ የሚገቡና በየዘርፎቹ የሚተገበሩ 35 የትኩረት አቅጣጫዎችን ለእያንዳንዱ ዘርፍ ለይተዉ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲተገበሩ ሰጥተዋል፡፡

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9
Gallery image 10

Tags

#Motri#coffee