ያረጀ  ቡናን ነቅሎ በአዲስ በመተካት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በኩታ ገጠም የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረዉ መቀጠሉ ተገለፀ
Back

ያረጀ ቡናን ነቅሎ በአዲስ በመተካት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በኩታ ገጠም የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረዉ መቀጠሉ ተገለፀ

ECTA
5 min read

ያረጀ ቡናን ነቅሎ በአዲስ በመተካት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በኩታ ገጠም የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረዉ መቀጠሉ ተገለፀ

‎ታህሳስ 06/2018 ዓ/ም

‎በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ኩታገጠም ያረጀ ቡናን ነቅሎ በአዲስ በመተካት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረዉ መቀጠሉ ተገልጿል።

‎በወረዳዉ ምርታማነታቸዉን የቀነሱ ያረጁ ቡናን ነቅሎ በአዲስ በመተካት ምርታማነትን ለማሳደግ በኩታ ገጠም የተጀመሩ ሥራዎች የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የይርጋጨፌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ቡኔ እና የወረዳ አስተባባሪዎችን ጨምሮ ተሳትፈዋል።

‎በወረዳዉ ቆንጋ ኩታገጠም 27 ሄክታር 46 አርሶአደሮች በማሳተፍ እየተሠራ እንዳለና በተመሳሳይ በስምንት ቀበሌያት ዘጠና ሦስት ነጥብ አምስት ሄክታር 213 አርሶአደሮችን በማሳተፍ በትኩረት እየተሠራ እንዳለ ተገልጿል።

‎ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረዳ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በኩታ ገጠም በተሠሩ ሥራዎች አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ እንዳለ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዞኑ የግብርና መምሪያ ኃላፊ የወረዳ አስተባባሪዎች እና ባለድርሻ አካላት በኢዲዶ የስፔሻሊቲ ቡና ጉብኝት አድርገዋል።

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8

Tags

#ECTA#coffee