ውይይት በንግድና ፕላን ሚኒስቴር
Back

ውይይት በንግድና ፕላን ሚኒስቴር

Motri
5 min read

በፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የተመራ የልዑካን ቡድን በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በመገኘት ከክቡር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን ሀገራዊ ተልዕኮ ይበልጥ ለማሳካት፣ የዘርፉን አሰራር ለማዘመን እና ቁልፍ የአገልግሎት መስኮች ራሳቸውን ችለው በጠንካራ ተቋማዊ ቁመና እንዲደራጁ ለማስቻል የሚያግዙ ሃሳቦች ዙሪያ መክረዋል።

በተለይም የሀገራችንን የንግድ ሥርዓት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በሚያሳድጉ፣ አስተማማኝ የቁጥጥር ሥርዓትን በሚገነቡ እና የገበያውን ጤናማነትና ፍትሃዊነት በሚያረጋግጡ ጠንካራ አደረጃጀቶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ክቡር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ይህ አጠቃላይ የተቋም ሪፎርም የሀገራችንን የንግድ ዘርፍ ለማዘመን፣ የኢኮኖሚ ዕድገታችንን ለማፋጠን እና የተገልጋዩን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተገልጿል።

ለተጨማሪ መረጃ

ኤክስ ገጽ:- https://x.com/MoTRI_Ethiopia

ቴሌግራም ገጽ፦ https://t.me/motri_gov_et

ዩትዩብ ቻናል፦ https://youtube.com/@ethiopian_ministry_of_trade...

ሊንክዲን ገጽ፦ https://www.linkedin.com/.../the-ministry-of-trade-and...

ዋትስ አፕ ቻናል፦ https://whatsapp.com/channel/0029VbCPQW4Fy725V6qBre0i

ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@motri71?_r=1&_t=ZS-94n5LSW3Ihs

ኢንስታግራም ፦ https://www.instagram.com/motriethiopia?igsh=MWVmdXNhcGc4OHBzYQ==

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8

Tags

#Motri#coffee