የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እና በሩሲያ ፌደሬሽን የሴንት ፒተርበርግ ኢንተርናሽናል መርከንታይል ኤክስቼንጅ (SPIMEX) በጋር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
Back

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እና በሩሲያ ፌደሬሽን የሴንት ፒተርበርግ ኢንተርናሽናል መርከንታይል ኤክስቼንጅ (SPIMEX) በጋር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

5 min read

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እና በሩሲያ ፌደሬሽን የሴንት ፒተርበርግ ኢንተርናሽናል መርከንታይል ኤክስቼንጅ በጋር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት አቶ መርጊያ ባይሣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሴንት ፒተርበርግ ኢንተርናሽናል መርከንታይል ኤክስቼንጅ (SPIMEX) ፕሬዝዳንት ኢጎር አርተሚይ ናቸው፡፡

አቶ መርጊያ ባይሣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በስምምነት ፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ እንደገለፁት የሴንት ፒተርበርግ ኢንተርናሽናል መርከንታይል ኤክስቼንጅ (SPIMEX) ልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣቱ እና ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር በጋራ ለመስራት በመስማማቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ስምምነቱ የንግድ እና የገበያ ትብብር ሂደቶችን እና በግብርና ምርቶችና በሌሎች ምርቶች ግብይት ዙሪያ ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ የሚያስችልና  የጋራ ጥቅምን መሠረት ባደረገ አግባብ ተፈጻሚ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

የሴንት ፒተርበርግ ኢንተርናሽናል መርከንታይል ኤክስቼንጅ (SPIMEX) ፕሬዝዳንት ኢጎር አርተሚይ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር በጋራ መስራታቸው በምርት ጥራትና ደረጃ አወጣጥ፣ በዓለም አቀፍ የምርቶች ዋጋ እና ውጤታማ የግብይት ሥርዓት በመፍጠር የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ከምርቶቻቸው ትክክለኛ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የሚያስችል ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ተቀራራቢ የሆነ የግብይት ሥርዓት እንዳላቸው የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ እነዚህን ሥራዎች፣ በሥልጠናና በተሞክሮ ልውውጥ በማሳደግ በዓለም ገበያ ተመራጭ የግብይት ማዕከል ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት አድርገናል ብለዋል፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የአሰራር ሥርዓቶች በኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ በአቶ ዳዊት ሙራ በኩል ቀርቦ ገለጻ የተደረገበት ሲሆን የሴንት ፒተርበርግ ኢንተርናሽናል መርከንታይል ኤክስቼንጅ ዋና ዋና ስኬቶችና የአሰራር ሥርዓቶች በፕሬዝዳንቱ አማካይነት ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል፡፡

በመጨረሻም ቡድኑ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የኦን ላይን የግብይት ማዕከልንና የቡና ቅምሻ ላቦራቶሪን ጎብኝተዋል፡፡

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9

Tags

#ethiopian commodities exchange#ecx#spimex