Spices Supplied to Central Market
Back

Spices Supplied to Central Market

ECTA
5 min read

19 ሺህ 600 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 19 ሺህ 600 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀረበ።

የክልሉ ሻይ፣ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት መኩሪያ እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት 21 ሺህ ቶን የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ 19 ሺህ 600 ቶን ምርት ማቅረብ ተችሏል።

በክልሉ ኮረሪማ፣ ዕርድ እና ዝንጅብል በስፋት እንደሚመረቱ ጠቅሰው÷ አሁን ላይ የቁንዶ በርበሬ ምርት በልዩ ትኩረት በመልማት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እየሆነ ይገኛል ብለዋል።

ወደ ግብይት የሚገቡት የቅመማ ቅመም ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፈላጊ በመሆናቸው የማልማት አቅምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም ገቢውን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱንም አመልክተዋል።

(ኤፍ ኤም ሲ)

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3

Tags

#ECTA#coffee