የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እያሰገነባው ያለውን ባለ 3B+G+35+T ወለል ሕንጻ ግንባት የደረሰበትን የሥራ ደረጃ በአካል በመገኘት ገምግመዋል።
በጉብኝታቸውም የግንባታ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ የተመለከቱ ሲኾን የግንባታ ሥራው በተቀመጠለት ጊዜና ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ የሚያስችሉ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባና የምርት ገበያው አመራሮች ከፍተኛ ክትትል ማድረግ እንዳለባቸውና አማካሪ ድርጅቱና የግንባታ ሥራ ተቋራጩ ጊዜ የለኝም በሚል መንፈስ ያላቸውን አቅም ሁሉ አሟጠው በመስራት ክረምቱን የቀደመ ሥራ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የዘመናዊ ግብይት ሥርዓቱ የሚያስገነባው ሕንጻ ለሀገራችን ብቻ ሳይኾን ለአህጉራችንም የዘመናዊ ግብይት ሥርዓትና የሀገራችን ብልጽግና ማሳያ ነው።