ፕሬስ ሪሊዝ እንደደረሰ በጥቅም ላይ የሚውል
Back

ፕሬስ ሪሊዝ እንደደረሰ በጥቅም ላይ የሚውል

ECTA
5 min read

ጥቅምት 05/2018

ኢ/ቡሻ/ባለስልጣን

በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት 151,969.41 ቶን ቡና በመላክ 622.5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 113,542 ቶን (ከዕቅዱ 75%) በመላክ 762.75 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር (ከዕቅዱ 123%) ገቢ ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 243.73 ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር (47%) ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡  

በ2018 በጀት ዓመት ሶስት ወራት የተላከዉ ቡና በመዳረሻ ሀገራት ሲታይ ጀርመን በመጠን 20,793.14 ቶን (18%) እና በገቢ 138.18 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (18%) ድርሻ፣ ሳዉድ አረቢያ በመጠን 16,088.45 ቶን (14%) እና በገቢ ደግሞ 102.18 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (13%) ድርሻ እንዲሁም ቤልጅዬም በመጠን 13,910.92 ቶን (12%) እና በገቢ 93.45 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር (12%) አፈፃፀም በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡ የቀሩ መዳረሻዎች በ2018 ገቢ ቅደም ተከተል 4ኛ ቻይና፣ 5ኛ አሜሪካ፣ 6ኛ ደ.ኮሪያ፣ 7ኛ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ፣ 8ኛ ጃፓን፣ 9ኛ ጣልያን  እና 10ኛ ራሽያ ፈደሬሽን ሲሆኑ ከ1 እስከ 10 ያሉት በአጠቃላይ በመጠን 80% እና በገቢ 79% የዉጪ ምንዛሪ ግኝት ይሸፍናሉ፡፡

Tags

#ecta