የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ከኢጋድ ዋና ጸሐፊ ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በመሆን ጅግጅጋ ገቡ።
ግንቦት 08/2018 ዓ.ም (ጅግጅጋ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ እና የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (IGAD) ዋና ጸሐፊ ክቡር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለማከናወን አመሻሹን ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።
ልዑኩ በዊልዋል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ፣ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ደማቅና ወንድማዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በዊልዋል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ፣ ለሥራ ኃላፊዎችና ለተከበሩ የሀገር ሽማግሌዎች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አክለውም የሶማሌ ክልል በእምቅ የእንስሳት ሀብቷ ለሀገራችን የወጪ ንግድ ዕድገት ያላትን ከፍተኛ አቅምና ታላቅ የእንግዳ ተቀባይነት እሴት አድንቀዋል።









