መስራት እና ውጤት ማምጣት ያሸልማል!!
Back

መስራት እና ውጤት ማምጣት ያሸልማል!!

Ethiopian Coffee And Tea Authority
5 min read

መስራት እና ውጤት ማምጣት ያሸልማል!!

አገራችን በተከታታይ 4 አመታት አኩሪ የሆነ የቡና ኤክስፖርት ግኝቶችን አስመዝግባለች። ዘንድሮም በታሪካችን የመጀመሪያ የሆነውን ኤክስፖርት አፈጻጸም በመጠንም፣ በገቢም ማግኘት ችለናል።

በተከታታይ ላስመዘገብነው ድል በተለይ ደግሞ የዘንድሮ አመት ውጤታችን በክቡር ጠ/ሚኒስትራችን የላቀ እውቅና እና አድናቆት አጎናፅፎናል። ለዚህም ማበረታቻ ይሆነን ዘንድ አንድ ራሳቸው የሚጠቀሙበትን እጅግ ዘመናዊ ኒሳን ፓትሮል ለመሸለም ችለናል።

ሽልማቱ ለላቀ ጥረት፤ ሽልማቱ ለላቀ ትጋት የሚያነሳሳን ነው። ሽልማቱ የሁሉ ባለድርሻ አካላት ርብርብ እና ውጤት ነው። ሽልማቱ የሁላችን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልፋት እና ድካም ውጤት ነው። በመሆኑም እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን። 

አሁንም በጋራ እንችላለን!!

አዱኛ  ደበላ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳ/ር

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2

Tags

#ecta#coffee#abiy