ለተመረጡ  ስፔሻሊቲ  ቡና አምራች  ወረዳዎችና  ማህበራት  በጥራት  ላይ  ያተኮረ  የቡና ምርትና ምርታማነት  ስልጠና  እየተሰጠ ነው ፡፡
Back

ለተመረጡ ስፔሻሊቲ ቡና አምራች ወረዳዎችና ማህበራት በጥራት ላይ ያተኮረ የቡና ምርትና ምርታማነት ስልጠና እየተሰጠ ነው ፡፡

ECTA
5 min read

በስፔሻሊቲ ቡና ጥራት ምርትና   ምርታማነት ዙሪያ  እየተሰጠ  ያለውን  ስልጠና በንግግር የከፈቱት በኢትዮጵያ  ቡናና ሻይ ባለስልጣን  ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የቡና ሻይና  ቅ/ቅመም ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታጋይ ኑሩ  ናቸው፡፡

አቶ ታጋይ ኑሩ  ለሰልጣኞቹ  እንዳስገነዘቡት  ስልጠናው በቡና ጥራት አጠባበቅ ምርትና ምርታማነትን  ማሳደግ  ያለመ  መሆኑን  ገልጸው  የቡና  ጥራት  ምርትና ምርማነት  ሲሻሻል  እና  ሲያድግ የቡና አምርች   አርሶ አደሩ ህይወትና የኑሮ ደረጃ   ይሻሻላል ይለወጣል ያድጋልም፡የሃገራችንም ኢኮኖሚ  በአንጻሩ   ያድጋል በውጭ  ገበያ  ያለው የቡና ተፈላጊነትም ያድጋል   ብለዋል ፡፡ አቶ ታጋይ ኑሩ ንግግራቸውን  በመቀጠል ላልተገባ ጥቅም ለማግኘት ቡናን ከባእድ ነገር ጋር  በመቀላቀል የቡናችንን ደረጃ  እና  ዋጋ በገበያው ዋጋ የሚያሳጣ  ተግባር የሚፈጽሙ አካላት  እንደሉና እነዚህን አካላት አርሶ አደሩ  ባለሙያውና በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላትና  የስራ  ሃላፊዎች  በመከታተል  ከደርጊታቸው  እንዲቆጠቡ ማድረግ  ይገባል ብለዋል፡፡

እንደ አቶ  ታጋይ ማብራሪያ በኦሮሚያ ክልል 70 በመቶ ፤ ደቡብ ምእራብ  ኢትዮጵያ ክልል 13 በመቶ፤ የሲዳማ ክልል 3  በመቶ ከአጠቃላይ  የሃገራችንን የቡና ምርት ለማእከላዊ ገበያ እንደሚያቀርቡ ገልጸው የሲዳማ   ክልል የቡናን ጥራት በማስጠበቅ እና ለውጭ ገበያ ተወዳዳሪነቱን በማሳደግ በአለም ገበያ  ካሉት የሃገራችን ቡና   አምራች  አካባቢዎች የአንበሳውን ድርሸ በመውሰድ ትልቁን የውጭ ገቢ ለሃገሪቱና ለአምራች አርሶ አደሩሶ እያስገኘ  ይገኛል  ካሉ በሁዋላ  ከዚህ  ክልል ትምህርና ተሞክሮ በመውሰድ ሌሎችም  ቡና አምራች  ክልሎችና  አካባቢዎች በቁጭት በመነሳሳት  የበቡና ምርትና ጥራት  በማጠበቅ በቡናው  ገበያ  ተወዳዳሪነታችሁን በማሳደግ ለአርሶ አደሩ ኑሮ መለወጥና ለሃገራችሁ ኢኮኖሚ እድገት  መስራት ይጠበቅባችኋል  በማለት ለሰልጣኖች በአጽንኦት አስገንዝበዋል ፡፡

ስልጠናው በዋናነት በስፔሻሊቲ  ቡና ምርት ጥራትና ደረጃ አጠባበቅ፤ በቡናው ገበያ እንዴት ተወዳዳሪ እና ተመራጭ መሆን  እንደሚቻል፤ በቡና ዘር መረጣ እና አዘገጃጀት በቡና በሽታ መከላከልና የቡና ምርትና ጥራት የሚቀንሱ ተባዮች መከላከልና ቁጥጥር፣ በቡና ክብካቤና አያያዝ አዘገጃጀትና  ክብካቤ፤ የቡና ተክል ልማትና ክብካቤ እና ክትትል፤ በስፔሻሊቲ  ቡና አመራረት በቡና ገበያና ግብይት  በሚሉ አንኩዋር ጉዳዮች  እየተሰጠ  ይገኛል፡፡ ስልጠናው  ከዛሬ  መስከረም 23 ቀን  ጀምሮ   ለሶስት ቀናት ከኦሮሚያ  እና ከደቡብ ምእራብ  ኢትዮጵያ  የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ለተውጣጡ ሰልጣኞች እንደሚሰጥ  ከአቶ ቦንሳ መርጋ  በኢትዮጵያ ቡናናሻይ ባለስልጣን  የስትራቴጂክ ጉዳዮች  ስራ አስፈጻሚ ለመረዳት ተችሏል  ፡፡ በስልጠናው ከ130 በላይ ሰልጣኖች እየተሳተፉ ይገኛሉ ፡፡

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#coffee#training#speciality