ለህጻናት፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋውያን መብቶች መከበር እና ሃላፊነትን የሚወጣ   ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
Back

ለህጻናት፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋውያን መብቶች መከበር እና ሃላፊነትን የሚወጣ   ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ECTA
5 min read

ለህጻናት፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋውያን መብቶች መከበር እና ሃላፊነትን የሚወጣ   ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ታህሳስ 01/2018

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞችና ዛሬ  ታህሳስ 1/2018 ዓ/ም   አለማቀፍ የህጻናት፣ የአረጋውያን፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ የጸረ ጾታዊ ጥቃት እንዲሁም የጸረ ኤች አይ ቪ ቀናቶችን በጋራ እና በድምቀት አክብረው ውለዋል∶∶

እነዚህ ቀናቶች ደግሞ ‹‹ጥበቃና የመጫወት መብት ለሁሉም ህጻናት››፤ ‹‹የአካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት  ለተሻለ ማህበራዊ እድገት››፤  ‹‹ጥቃትን  የማይታገስ  ማህበረሰብ  ለትውልድ ግንባታ››፤ ‹‹የአረጋውያን  ደህንነትና መብቶች በመጠበቅ ሁለንተናዊ ሃላፊነታችንን እንወጣ›› እንዲሁም ‹‹Overcoming Disruption, Transforming the AIDS Response›› የሚሉ መሪ ቃሎች የነበራቸው ሲሆን በተለያዩ  ፕሮግራሞች ደምቆ ውሏል ፡፡

ክቡር አቶ ሻፊ ኡመር  በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የገበያ ልማትና ቁጥጥር ዘርፍ ሃላፊ የእለቱን ፕሮግራም በንግግር በከፈቱበት ወቅት፣ ‹‹አካል ጉዳተኞችን  በማሀበራዊ እና በልማት በፖለቲካዊ ዘርፍ ተካታች ሆነው የበኩላቸውን ለሃገራችን አበርክቶ እንዲያደርጉ እንዲሁም ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሁላችንም  ሃላፊነት በመወጣት አጋርነታችን  በተግባር ማሳየት ይገባል›› ብለዋል ፡፡

በእለቱ  በህጸናት መብቶችና አለም አቀፍ ኮንቬንሽን፤ በአረጋውያን  መብት ጥበቃና የሴቶችን ጾታዊ ጥቃት አካል ጉዳተኝነትና በህብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትና ተካታችነት  ዙሪያ የሚያጠነጥን ሰነድ በቀረበበት ወቅት ለህጻናት፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን  መብቶች መከበር  እና ሃላፊነቱን  የሚወጣ  ማህበረሰብ መገንባት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ፍጹም  መንገሻ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ስራ አስፈጻሚ ናቸው ፡፡

በእለቱ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ቢሮ በመጡ የጤና ባለሙያዎች murburg  virus ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያና ትምህርታዊ ገለጻ  በማድረግ ለሰራተኛው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፊዚዮቴራፒ ህክምና በሴቶች፣  ህጻናት፣ አረጋውያን እንዲሁም አካል ጉዳተኞች ሊኖረው የሚችለውን ሚና በተመለከተም በባለሙያ የተደገፈ ማብራሪያ ቀርቧል∶∶

የእለቱ ፕግራም በተለያዬ  አዝናኝ  ድራማዎችና ግጥሞች  ደምቆ ውሏል∶∶

ሀብታሙ መብራቱ እንደዘገበው

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6
Gallery image 7
Gallery image 8
Gallery image 9
Gallery image 10

Tags

#ecta#coffee