ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮ ቻይና ወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
Back

ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ የኢትዮ ቻይና ወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ECTA
5 min read

በቡና ዘርፍ ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

‎መስከረም 28/2018 

አዲስ አበባ 

‎የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳ/ር ክቡር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር) የኢትዮ ቻይና ወዳጅነት ትብብር ኮሚቴን ዛሬ  በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። የልዑካን ቡድኑ በነበረው ቆይታ በጌዲኦ ዞን የሚገኙ ቡና አብቃይ አካባቢዎችን መጎብኘቱ የተገለፀ ሲሆን የቡና አቅራቢ ድርጅቶችና የህብረት ስራ ዩኒየኖችም ጋር ውጤታማ ቆይታ እንደነበራቸው ተናግረዋል።

ኮሚቴው የኢትዮጵያን ቡና ለቻይና ገበያ በማስተዋወቅ ረገድ በስፋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ መሆኑ በውይይቱ ወቅት የተገለፀ ሲሆን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ማድረግን ጨምሮ  የተሻለ ገበያና ቀጥተኛ የገበያ ትስስር ለመፍጠር እንዲሁም ፋይናንሻል ድጋፍ በማድረግም በኩል እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተወስቷል። በቅርቡ ደግሞ ገዢ ኩባንያዎችን ያቀፈ የልዑካን ቡድን እንደሚመጣ ተጠቁሟል።

በቻይና የተለያዩ ግዛቶችም የኢትዮጵያን ቡና ለማስተዋወቅ የሚያስችሉ የፕሮሞሽን ተግባራት እንደሚከናወኑና በቻይና የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑንም በውይይቱ ወቅት አብራርተዋል።

ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ ‎ዶ/ር አዱኛ በበኩላቸው የኢትዮ ቻይና ወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የአገራችንን ቡና በማሳው በመገኘት መመልከት በመቻላቸው ያላቸውን አድናቆት የገለፁላቸው ሲሆን ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ካላት የተጠናከረ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ባሻገር በቡናው ዘርፍ ከጊዜ ወደጊዜ እየታየ ያለው ወዳጅነት እና ትብብር የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልከው 

የቡና ምርት እያደገ መሆኑን እና በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን ቡና ከሚገዙ አገራት መካከል ቻይና ከዋናዎቹ አስሮቹ ተርታ መሠለፏ ለዚህ ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል። ለወደፊቱም ይህ የሁለትዮሽ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ እና ገዢ ገልፀው ኩባንያዎች ለሚያስፈልጋቸው ማናቸውም ድጋፍ መንግስት የሚጠበቅበትን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይልም አረጋግጠውላቸዋል።

‎  

Gallery

Gallery image 1
Gallery image 2
Gallery image 3
Gallery image 4
Gallery image 5
Gallery image 6

Tags

#china#coffee